የወንዶች እና የሴቶች ፕሪምየር ሊግ እጩ ኮከቦች ታውቀዋል

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በስሩ በሚያካሂዳቸው ሊጎች ላይ ምርጥ አቋም ላሳዩ ተጫዋቾች በተናጠል በየሊጎቹ የመጨረሻ ጨዋታዎች ላይ የሚሰጠው የሽልማት ስነስርአት በዘንድሮው የውድድር ዘመን ተቀይሮ የሁሉንም ሊጎች ኮከቦች በጋራ ለመሸለም መወሰኑ የሚታወስ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለቱም ጾታዎች ላይ ለሽልማቱ የታጩ ተጫዋቾች የታወቁ ሲሆን በኮከብ ተጫዋችነት እና ኮከብ ግብ ጠባቂነት ሶስት ተጫዋቾች ለእጩነት ቀርበዋል፡፡

የወንዶች ፕሪምየር ሊግ

በኮከብ ተጫዋች ዘርፍ ከቻምፒዮኑ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሁለት ተጫዋቾች ተካተዋል፡፡ የአምናው ኮከብ አስቻለው ታመነ እና አማካዩ ምንተስኖት አዳነ በእጩዎች ዝርዝር የተካተቱ ሲሆን የሲዳማ ቡናው አማካይ ሙሉአለም መስፍን ሌላው በእጩነት የተካተተ ተጫዋች ነው፡፡

በግብ ጠባቂ ዘርፍ ለ5 ተከታታይ አመታት ኮከብ ተብሎ የተመረጠው የቅዱስ ጊዮርጊሱ ሮበርት ኦዶንካራ በእጩነት  ሲካተት የመከላከያው አቤል ማሞ እና የሲዳማ ቡናው ለአለም ብርሀኑ ሌሎች በእጩነት የተካተቱ ግብ ጠባቂዎች ናቸው፡፡

የሴቶች ፕሪምየር ሊግ

በተጫዋች ዘርፍ ሰናይት ቦጋለ እና ብሩክታዊት ግሮማ ከሊጉ ቻምፒዮን ደደቢት ሲካተቱ የንግድ ባንኳ አማካይ ዙለይካ ጁሀድ ሌላዋ በእጩዎች ዝርዝር የተካተተች ተጫዋች ናት፡፡

በግብ ጠባቂ ዘርፍ የሀዋሳ ከተማዋ ትዕግስት አበራ ፣ የድሬዳዋ ከተማዋ ታሪኳ በርገና እና የአዳማ ከተማዋ ሳሳሁልሽ ስዩም ሶስቱ እጩዎች ሆነዋል፡፡

 ሌሎች ሊጎች

ከወንዶች እና ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ውጪ የሚገኙት ሌሎች ምርጫዎች በሌሎች ኮሚቴዎች እየተከናወኑ ሲሆን የከፍተኛ ሊግ ፣ ከ17 አመት በታች ፕሪምየር ሊግ እና ከ20 አመት በታች ፕሪምየር ሊግ እጩዎች ከከፍተኛ ሊጉ መጠናቀቅ በኋላ በጋራ ይታወቃሉ ተብሏል፡፡ በተመሳሳይ በሌላ ኮሚቴ ስር እየተከናወነ የሚገኘው የአንደኛ ሊግ ምርጫ እጩዎችም በድሬዳዋ ከሚደረገው የማጠቃለያ ውድድር በኋላ ይፋ እንደሚሆን ታውቋል፡፡

3 Comments

  1. Echu beregnoches lemen hariston hesus echu alonem ahune guboale aydel ere federeshen ahunem asyekakel

  2. kokob gib agbi kehonu kokob techawach yameltachewal malet new? Getaneh ena Loza mirt techawachnet ayigebachewm? atleast echu ayihonum??

  3. diredawa lay ye andegna league matekaleya yalachut neger algebagn? malet yetignawu newu? keye midibachewu andegna yemiwotu kefitegna league aygebum?

Leave a Reply