‹‹ የህዝባችን ድጋፍ ውጤት እንድናመጣ ትልቁን ድጋፍ አድርጎልናል ›› ዮሴፍ ተስፋዬ

የብሄራዊ ቡድኑ የቡድን መሪ አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ ከዛሬው ድል በኋላ ለጋዜጠኞች አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ የቡድን መሪ የሰጡትን አስተያየት እንዲህ አሰናድተነዋል፡፡

 

‹‹ ውጤቱ የህዝብ ነው፡፡ እኛም ለውጤቱ ስራዎችን ብንሰራም የህዝባችን ድጋፍ ውጤት እንድናመጣ ትልቁን ድጋፍ አድርጎልናል፡፡ እስካሁን ለነበረን ቆይታ እና በሁለቱ ጨዋዎች ላደረጋችሁልን ድፈጋፍ ከፍ ያለ ምስጋና እናቀርባለን፡፡ እንኳን ደስ አላችሁ፡፡ ››

‹‹ የባህርዳር ቆይታችንን ማክሰኞ አገባደን ወደ አዲስ አበባ እመለሳለን፡፡ ከዚያም የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለተጫዋቾቹ ቃል የገባውን ሽልማት ይሰጣል፡፡ በመጪው ረቡእ ደግሞ ወደ ሃዋሳ ተጉዘን ከኬንያ ጋር ለምናደርገው ጨዋታ ዝግጅታችንን እንቀጥላለን፡፡ በሃዋሳ ለአንድ ሳምንት ቆይተን ጨዋታው 4 ቀን ሲቀረው ወደ ኬንያ እናመራለን፡፡ ››

‹‹ ሀሙስ እና አርብ የኢትዮጵያ ዋንጫ ጨዋታዎች የሚካሄዱ ሲሆን ሀሙስ ጨዋታ የሚያደርጉ ተጫዋቾች አርብ ብሄራዊ ቡድኑን ይቀላቀላሉ ፣ አርብ ጨዋታ የሚያደርጉ ተጫዋቾች ደግሞ ቅዳሜ ወደ ሀዋሳ ያመራሉ፡፡ ››

ያጋሩ