የዋልያዎቹ የመሃል ተከላካይ ሳላዲን በርጊቾ ከዛሬው ድል በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጠው አስተያየት ደጋፊውን አመስግኗል፡፡ ስለ ጨዋታውም አጠር ያለ አስተያየት ሰጥቷል፡፡ እኛም የሳላዲንን አስተያየት እንዲህ አቅርበነዋል፡፡
‹‹ ውጤቱ አስደስቶናል፡፡ በሜዳችን እንደመጫወታችን መጠን በ2 ግብ ልዩነት ማሸነፋችን የመልሱን ጨዋታ ያቀልልናል ብዬ አስባለሁ፡፡››
‹‹ ደጋፊው 90 ደቂቃ ሙሉ ሲያበረታቱን ነበር፡፡ ካለፈው ጨዋታ ጀምሮም ከጎናችን ነበሩ፡፡ ደጋፊውን ማመስገን እፈልጋለሁ፡፡››
‹‹ ሁሉም ተጫዋቾች ውጤት የተጠሙ ነበሩ፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጠ ብንዘጋጅም ከአስቻለው ጋር ጥሩ ጥምረት መፍጠር ችለናል፡፡ ››
‹‹ በባለፈው ጨዋታ ሌሶቶዎች በታክቲኩ የተደራጁ ነበሩ፡፡ ቀጥታ የመጡትም ተከላክሎ ውጤት ይዞ ለመውጣት ነበር፡፡ ኬንያዎች ግን አጥቅተው ለመጫወት ያደረጉት ጥረት እኛን ጠቅሞናል፡፡ ››
ያጋሩ