የኢትዮጵያ የክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ነገ በይፋ ሲከፈት የሊግ ውድድሮች ከተጀመሩ በኋላ እስከ 15ኛው ቀን ድረስም ክለቦች በቃል ደረጃ የተስማሟቸውን ተጫዋቾች በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን እየተገኙ በይፋ የሚያስፈርሙ ይሆናል፡፡
ካለፉት ጥቂት አመታት በተሻለ ዘንድሮ ከከፍተኛ ሊጉ በቀር የውስጥ ሊጎች ከሐምሌ 1 በፊት የተጠናቀቁ ሲሆን የተጫዋቾች ኮንትራት በአመዛኙ ሰኔ 30 ላይ የሚያልቅ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በርካታ ዝውውሮች በቀጣዮቹ ወራት የሚደሩ ይሆናል፡፡
በተጠናቀቀው የውድድር አመት የተለያየ እርከን ላይ የሚገኙ ሊጎች በተመሳሳይ ወቅቶች መጠናቀቅ ባለመቻላቸው በተለይ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ያደጉ ክለቦች ከሌሎቹ ክለቦች እኩል በገበያው ላይ መንቀሳቀስ አለመቻላቸው የሚታወስ ሲሆን ዘንድሮ አዳዲስ ያደጉ ክለቦች በተሻለ መልኩ ገበያው ላይ ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ሶከር ኢትዮጵያ የዝውውር መስኮቱን መከፈት በማስመልከት ከነገ ጀምሮ ለቀጣዮቹ ወራት ተአማኒ የሆኑ የዝውውር ዜናዎች ፣ ከዝውውር ጋር ተያያዥ የሆኑ ቃለ ምልልሶች ፣ ትንታኔዎች ፣ አስተያየቶች እና ዳሰሳዎች የምታቀርብ መሆኑን ከወዲሁ ትገልጻለች፡፡