የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የከፍተኛ ሊግ የመጨረሻ ሁለት ጨዋታዎች ላይ የቀን እና የሰአት ለውጥ ማድረጉ ታውቋል፡፡
ቀደም ብሎ በወጣው መርሀ ግብር ጨዋታዎቹ ሐምሌ 11 ቀን 2009 በ08:00 እና 10:00 ላይ የሚደረጉ ቢሆንም ጨዋታዎቹ የተሻለ ተመልካች እንዲያገኙ እና 08:00 ካለው የድሬዳዋ ሙቀት አንጻር ለጨዋታ አመቺ አይደለም በሚል በተለያዩ ቀናት እንዲደረጉ ተወስኗል፡፡
በዚህም መሰረት በመቀለ ከተማ እና ሀዲያ ሆሳዕና መካከል የሚደረገው ወደ ፕሪምየር ሊግ ለመግባት በሚደረገው ወሳኝ ጨዋታ በተመሳሳይ ቀን ሐምሌ 11 ቀን 2009 ሲደረግ ሰአቱ ግን ወደ 10:00 ተሸጋሽጓል፡፡ በቀጣዩ ቀን ሐምሌ 12 ደግሞ ምድባቸውን በቀዳሚነት ያጠናቀቁት ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና ጅማ ከተማ 10:00 ላይ የከፍተኛ ሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ይፋለማሉ፡፡