የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ የማጠቃለያ ውድድር ዛሬ በሁለት ጨዋታዎች ተጀመረ

የኢትዮዽያ አንደኛ ሊግ የማጠቃልያ ውድድር በድሬደዋ ከተማ አስተናጋጅነት ከፍተኛ ሊግ መግባታቸውን ባረጋገጡ ስድስት ቡድኖች መካከል የሚደረገው ውድድር በደማቅ ሁኔታ  ዛሬ ሲጀምር ቡታጅራ ከተማ ከየካ እንዲሁም ሀምበሪቾ ከ ሚዛን አማን ያደረጉት ጨዋታ በተመሳሳይ ውጤት 1 – 1 ተጠናቋል ።

በኢትዮዽያ ብሔራዊ መዝሙር የተጀመረው የመክፈቻ ስነ ስርአት የዕለቱ የክብር እንግዳ የሆኑት የኢትዮዽያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት አቶ ጁነይዲ ባሻ እና የድሬደዋ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ከድር ጁሀር እንዲሁም ሌሎች የክብር እንግዶች በመገኘት ከየቡድኖቹ ጋር ሰላምታ ተለዋውጠዋል ።

08:00 ላይ በጀመረው የምድብ ሀ ጨዋታ  ቡታጅራ ከተማ እና በየካ ጨዋታ ብዙ ባልተሳኩ የኳስ ቅብብሎች ምክንያት ቀዝቀዝ ብሎ ነበር የጀመረው ።  በ17 ኛው ደቂቃ ለታ ዋቅጅራ የበረኛውን አቋቋም አይቶ ከርቀት የመታው ኳስ የግቡ አግዳሚ ሲመልሰው እሸቱ በቀለ በግንባሩ ገጭቶ ለጨዋታ የመጀመርያ የጎል ሙከራም የመጀመርያ ጎል ሆኖ ለቡታጅራ ተመዝግቧል ።

ከጎሏ መቆጠር በኋላ ቡታጅራዎች ተጭነው በመጫወት ተጨማሪ ጎል በማስቆጠር መሪነታቸውን ማስፋት የሚችሉበትን አጋጣሚ ሳይጠቀሙበት ቀርተዋል ። በአንፃሩ በሂደት ወደ ጨዋታው የተመለሱት የካዎች በታምሩ ባልቻ አማካኝነት በሁለት አጋጣሚ የጎል እድል አግኝተው ሳይጠቀምበት ቀርቶ የመጀመርያው አጋማሽ በቡታጅራ 1 – 0 መሪነት ተጠናቃቋል ።

በሁለተኛው አጋማሽ ብዙም ሳቢ እንቅስቃሴ ባይታይበትም ቡታጅራዎች ከየካ በተሻለ የጎል ሙከራ አድርገዋል በተለይ ፍ/ማርያም ጫላ እና ዋኬኔ አዱኛ ያመከኑት የጎል እድል የሚያስቆጭ ነበር ። ጨዋታ ወደ መጠናቀቂያው ላይ አልፎ አልፎ ወደ ጎል ይደርሱ የበሩት የካዎች 84 ኛው ደቂቃ ላይ ብሩክ ቸርነት በግራ እግሩ አክሮ በመምታት ጎል አሰቆጥሮ የካዎችን አቻ ሊያደርግ ችሏል  ። ጨዋታውም በዚሁ ውጤት 1 – 1 ተጠናቋል ።

10:00 ላይ በቀጠለውና በምድብ ለ የሚገኙትን ሀምበሪቾ ከ ሚዛን አማን ባገናኘው ጨዋታ ተመልካችን ያዝናና በበርካታ የጎል ሙከራ የታገዘ ሲሆን በጨዋታው 12ኛ ደቂቃ ላይ ከቅጣት ምት የተመታውን ኳስ ግብ ጠባቂው የተፈውን ቢኒያም ጌታቸው ወደ ጎልነት ቀይሮት ሀምበሪቾን ቀዳሚ አድርጓል። ጨዋተው በጥሩ እንቅስቃሴ ቀጥሎ 25ኛው ደቂቃ ላይ ሰብረው የገቡት ሚዛን አማኖች በሙሴ እንደ ጎል አማካኝነት አቻ መሆን  ቻሉ። ሚዛን አማኖች ተጨማሪ ጎል የሚሆን አጋጣሚ አግኝተው ዘላለም መኮንን አምክኖታል ። ጨዋታውም 1 – 1 በሆነ ውጤት እረፍት ወተዋል ።

ከእረፍት መልስ ተጋግሎ በቀጠለው የሁለቱ ጨዋታ ሀምበሪቾ ተጭኖ የተጫወተ ሲሆን ጥሩ የሆነ አቋሙን በጨዋታው ላይ ያሳየው  የሀንበሪቾው አጥቂ  ቢንያም ጌታቸው ሁለት ጊዜ ግልፅ የሆነ የማግባት አጋጣሚ አግኝቶ ሳይጠቀምበት የቀረው። ሚዛን አማኖች በኩል  በዘላለም መኮንን የሞከረው ኳስ በሁለተኛው አጋማሽ የተፈጠሩ የጎል እድሎች ነበሩ። ጨዋታው መጠናቀቂያ 90ኛው ደቂቃ ላይ የሚዛን  አማኑ አበራ አየለ የሚዛን አማን ፍ/ቅ/ም ክልል  ውስጥ ተጨዋች በክርን ተማቶ ረዳት ዳኛውን ምልክት ያላዩት የዕለቱ ዳኛ ሚካኤል አርአያ ለአንድ ደቂቃ ያህል  ጨዋታው እየቀጠለ በለበት ሰአት የረዳት ዳኝውን ጥሪ ሰምተው አበራ አየለን በቀይ ካርድ አሶጥተውታል። ጨዋታው 1 – 1 በሆነ ውጤት ከተጠናቀቀ በኋላ ሀምበሪቾዎች ተጨዋቹ ቀይ በመመልከቱ ጥፋት በተሰራበት ቦታ ላይ ፍፁም ቅጣት ምት ሊሰጠን ይገባ ነበር በማለት ክስ አስይዘዋል።

ውድድሩ ሰኞ ሲቀጥል

08:00  መቂ ከተማ ከ ከየካ ክ/ከ

10:00   ደሴ ከተማ ከ ከ ሀምበሪቾ ከተማ የሚጫወቱ ይሆናል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *