ጉዞ ወደ ፕሪምየር ሊግ – መቐለ ከተማ ከ ሀዲያ ሆሳዕና | ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

 FT  መቐለ ከተማ  2-1  ሀዲያ ሆሳዕና 

16′ አማኑኤል ገብረሚካኤል 78′ ዮሴፍ ታዬ | 14′ እንዳለ ደባልቄ


ተጠናቀቀ!
ጨዋታው በመቀለ ከተማ አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡ መቀለ ከተማ ወልዋሎ እና ጅማን ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ለመጀመርያ ጊዜ አድጓል፡፡ 

ተጨማሪ ደቂቃ – 4

86′ መቀለ በጥብቅ መከላከል ኳሶችን ከግብ ክልላቸው እያራቁ ሲገኙ ሀድያዎች ጎል ፍለጋ በሙሉ ሀይላቸው ተጭነው እየተጫወቱ ይገኛሉ።

78′ ጎልልል!!!!

ዮሴፍ ታዬ በቅጣት ምት አሰቆጥሮ መቀለ ከተማን መሪ አድርጓል፡፡ 4 የሀድያ ሆሳዕና ተጫዋቾች የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክተዋል፡፡

75′ መቀለ ጫና ፈጥሮ እየተጫወተ ሲሆን ሀድያዎች በአንፃሩ ተዳክመው እየታዩ ይገኛል፡፡

73′ ኤርሚያስ ታደሰ መቀለዎች ያገኙትን ቅጣት ምት ወደ ጎል መትቶ ግብጠባቂው አስራት አወጣበት፡፡ ጥሩ የጎል ሙከራ!

70′ ጨዋታው በተቀዛቀዘ ሁኔታ ቀጥሏል፡፡ ሆኖም ሀድያ ሆሳዕናዎች በተሻለ ሁኔታ ጨዋታውን ተቆጣጥረው እየተጫወቱ ይገኛሉ።

57′ ሄኖክ አርፊጮ ከቅጣት ምት ያሻገረውን ሳምሶን ቆልቻ በግንባሩ የገጨው ኳስ ለጥቂት ሲወጣ ኳሱን በፍጥነት የጀመሩት መቀለዎች በአስራት ሸገሬ አማካኝነት የግብ እድል አግኝተው ለጥቂት ወደ ውጪ ወጥቶባቸዋል።

55′ በመጀመርያው አጋማሽ በሁለቱም ቡድኖች በኩል እንደተመለከትነው ያለ ጠንካራ ፉክክር እየተመለከትን አንገኝም።

50′ የተጨዋች ለውጥ መቀለ – ኤርሚያስ ታደሰ ወጥቶ ኃይሉ ገ/የሱስ ገብቷል።

46′ እንዳለ ደባልቄ በግምት 25 ሜትር ርቀት የመታውን ኳስ ግብ ጠባቂው ሶፎንያስ ሰይፈ አወጣበት።

ተጀምሯል!
መቀለ ከነማ የሀድያዎቹ አምበል ኄኖክ አርፊጮ እና ግብ ጠባቂው አስራት ሚሻሞ ተገቢ ያልሆኑ ተጨዋቾች ናቸው በማለት ክስ አዚዘው። ጨዋታው ተጀምሯል።


እረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ 1-1 ተጠናቋል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ – 4

40′ ጨዋታው በተደጋጋሚ በሁለቱም ቡድኖች በኩል በሚሰሩ ጥፋቶች እየተቆራረጠ ይገኛል። በጨዋታውም የመጀመርያ ቢጫን የመቀለው ተመስገን አዳሙ ተመልክቷል።

33′ በአንድ ሁለት ቅብብል ኳሱን ተቆጣጥረው እየተጫወቱ ያሉት ሆሳዕናዎች ወደ ጎል በመድረስ የተሻሉ ቢሆኑም መቀለዎች በፍጥነት ወደ ማጥቃት በመሸጋገር አደጋ እየፈጠሩ ይገኛሉ፡፡

27′ አሚኖ ነስሮ ከግራ መስመር የተሻገረውን የቅጣት ምት ኳስ በግንባሩ ገጭቶት ለጥቂት አግዳሚውን ታኮ ወጣበት።

20′ ሀዲያ ሆሳዕና በእንዳለ እና አምራላ አማካኝነት ጥሩ የግብ እድል አግኝተው ሳይጠቀሙበት ቀርተዋል፡፡ ዝናቡ መልሶ መዝነብ ጀምሯል፡፡

ጎልልል!!!
አስገራሚ ምላሽ! አማኑኤል ገብረሚካኤል በግምት ከ30 ሜትር አክርሮ በመምታት ግሩም ጎል አስቆጠረ፡፡

ጎልልል!!!!
እንዳለ ደባልቄ በግል ጥረቱ ተጠቅሞ ሀዲያ ሆሳዕናን ቀዳሚ ያደረገች ጎል አስቆጥሯል፡፡

13′ ጨዋታው በአስገራሚ የደጋፊ ድባብ በፈጣን እንቅስቃሴ እልህ በተሞላበት መንገድ ተጋግሎ ቀጥሏል።

8′ ጨዋታው ከቆመበት ቀጥሏል፡፡

* ዝናቡ ማባራቱን ተከትሎ የዕለቱ ዳኞች ወደ ሜዳ ገብተው በማየት 8ኛው ደቂቃ ላይ የተቋረጠውን ጨዋታ እንዲጀምር ቡድኖቹን በመጥራት ላይ ይገኛሉ።

8′ ጨዋታው በከባድ ዝናብ ምክንያት ተቋርጧል፡፡ ተጫዋቾቹም ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል፡፡

3′ ሀድያ ሆሳህና ከማዕዘን በተሻገረ ኳስ ጎል ቢያስቆጥሩም ከጨዋታ ውጪ ነው በማለት የዕለቱ ዳኛ ሽረውታል።

ተጀመረ!

ጨዋታው በዝናብ ታጅቦ ተጀምሯል፡፡

09:55 ሰሞኑን ከፍተኛ ሙቀት ይስተናገድባት የነበረችው ድሬደዋ በዚህ ሰአት በአስገራሚ ሁኔታ መጠነኛ ዝናብ እየዘነበ ይገኛል፡፡

09:50 ጨዋታው ወደ መጀመሩ ደርሷል በስቴዲዮሙ ውስጥ ያለው ድባብ እጅግ አስገራሚ ነው። ቡድኖቹም ልምዳቸውን አጠናቀው ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል ።
09:30 ሁለቱም ቡድኖች ወደ ሜዳ በመግባት የማሟሟቂያ ልምምዳቸውን እየሰሩ ይገኛሉ ።

የዕለቱ ዳኞች እና ኮሚሽነር 

ዋና ዳኛ – በአምላክ ተሰማ 

ረዳት ዳኞች – ተመስገን ሳሙኤል እና ክንፈ ይልማ

ኮሚሽነር – ኃይለመልዓክ ተሰማ 

የመቐለ ከተማ አሰላለፍ

30 ሶፋንያስ ሰይፈ ፣ 2 አሌክስ ተሰማ ፣ 3 ተመስገን አዳሙ ፣ 22 ኤርምያስ ታደሰ ፣ 15 ዮሴፍ ሀይሉ ፣ 17 ሐብታሙ ተከስተ ፣ 10 ያሬድ ከበደ ፣ 6 አስራት ሸገሬ ፣ 12 ዜናው ፈረደ ፣ 11 አማኑኤል ገብረሚካኤል

ተጠባባቂዎች

1 ምሕረተአብ ገብረህይወት ፣ 22 ኤርሚያስ ታደሰ ፣ 23 ኃይሉ ገብረየሱስ ፣ 4 ሳምኤል መረሳ ፣ 19 ሀዱሽ አወጣህኝ ፣ 21 ክብሮም አስሐላሽ ፣ 7 ግርማይ ምሩፅ ፣ 5 ጌድዮን ታደሰ

የሀዲያ ሆሳዕና አሰላለፍ

1 አስራት ሚሻሞ ፣ 4 በረከት ወ/ዮሐንስ ፣ 12 ዕርቂሁን ተስፋዬ ፣ 8 አሚኖ ነስሮ ፣ 17 ሄኖክ አርፊጮ ፣ 25 አማኑኤል አሽሊ ፣ 14 አምራላ ደልታታ ፣ 11 ካሳሁን ገረመው ፣ 10 ቢንያም ታዬ ፣ 18 እንዳለ ደባልቄ ፣ 23 ሳምሶን ቶልቻ

ተጠባባቂዎች

99 ሐብቴ ከድር ፣ 19 አየለ ተስፋዬ ፣ 24 መልካሙ ፉንዱሬ ፣ 26 ዋቴሮ ኤልያስ ፣ 27 አበው ታምሩ ፣ 16 ቢንያም ገመቹ ፣ 21 ዱላ ሙላቱ

ጤና ይስጥልን ክቡራት እና ክቡራን!

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የመለያ ጨዋታ (Playoff) ዛሬ መቐለ ከተማ ከ ሀዲያ ሆሳዕና የሚያደርጉት ጨዋታ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና ጅማ ከተማን ተከትሎ ወደ ፕሪምየር ሊግ የሚያድገው 3ኛ ክለብ ይታወቃል፡፡ ይህንን ተጠባቂ ጨዋታም ዳንኤል መስፍን ከስፍራው እያንዳንዷን ክስተት በቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት ወደ እናንተ ያደርሳል፡፡

መልካም ቆይታ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር!

18 Comments

 1. You r one of a negative thinker’s ,How can you have made a judgment before the game playoff ?
  Any way the game was finished by mekelle 2 -1 . Ende ahya sayhon ende sew asib .

  1. ante yhonk abebe beso bela nger ante lam chawatawun satay bsme sme tdnfalh enda mekelle l PL ymaymtn budn nawu

 2. ደስ ብሎናል ጎልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልል መቐለ ወደ ፕሪሜርሊጉ ተቀላቀለ …

 3. ar hadiyoch men nekachu gole gole gole enflgalen mndnawu esu mashnf ged nawu

 4. እናንተ ብቻ
  ትችት የኢትዮጺያ እግር ኳስ ይቀይረዋል አላስብም
  1.prime sport (በትችት 1ኛ) – ባለጌ
  2.tribun sport (ትንሽ ይሻላል)
  3.sport 365

 5. አሰላለፍ ላይ የመቐለ ተጨዋቾች 10 ናቸው እንዴ?

 6. hult ymymtatnu clubocha nachwu eytchawtu yalut hadiya hossana kalalfe y ethiopia Pl y snfoch wuddr mhonu aykrm dgntu asamro yhen poleticega club mashnafu nawu

 7. the page not comfortable to refresh
  we are refreshing unwanted data
  you know that
  make it specified for LIVE only

Leave a Reply