ዳዊት እሰጢፋኖስ ወደ ድሬዳዋ ከተማ ተመልሷል

በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት በርካታ ተጫዋቾችን በማዘዋወር ቀዳሚ የሆነው ድሬዳዋ ከተማ ዳዊት እስጢፋኖስን በድጋሚ ሲያስፈርም የአራት ተጫዋቾችን ውል አድሷል፡፡

በ2008 በድሬዳዋ ከተማ ያሳለፈው ዳዊት እስጢፋኖስ የተጠናቀቀው የውድድር ዘመንን በኢትዮ እሌክትሪክ ካሳለፈ በኋላ በድጋሚ ድሬዳዋ ከተማን በአንድ አመት ውል ተቀላቅሏል፡፡

አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው የተከላካይ መስመራቸውን በዝውውር መስኮቱ ያጠናከሩ ሲሆን በማጥቃት እንቅስቃሴው ደካማ የነበረውን ቡድን ለማሻሻል ዳዊትን አስፈርመዋል፡፡

ክለቡ ተሰፋዬ ዲባባ ፣ ፍቃዱ ወርቁ እና በላይ አባይነህን ጨምሮ ውላቸውን ያጠናቀቁ በርካታ ተጫዋቾችን ውል ያላደሰ ሲሆን በረከት ሳሙኤል ፣ ይሁን እንደሻው ፣ ሱራፌል ዳንኤል እና ሳምሶን አሰፋ ለተጨማሪ ሁለት አመታት አድሰዋል፡፡

ድሬዳዋ ከተማ በዝውውር መስኮቱ ለማስፈረም ከተስማማቸው ተጫዋቾች መካከል ሞገስ ታደሰ ሳይፈርም የቀረ ሲሆን ወደ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሊያመራ ይችላል ተብሏል፡፡ ለወልዲያ መፈረሙ የተረጋገጠው ብሩክ ቃልቦሬ በቅድሚያ ለድሬዳዋ ፈርሞ ነበር በሚል ለፌዴሬሽኑ ክስ ማስገባቱም ታውቋል፡፡

2 Comments

  1. dawit negade eyehone yimeslegnal kileb eyekeyayer birr magbesbesun teyayzotal.dire kenema ye 1 amet contrat masferem yiker endezi budin ayseram.tadagiwochn masadeg yeteshale new.ewnet lemenager yemiwetaw genzeb betam yasasibal.ye dire kenema yebelay halafi ato ADEM FARAH tiretih yasmesegnihal bertalin.

  2. የኢትዮጵያ አሰልጣኞች ወጣቶች ላይ አይሰሩም ; ሁል ጊዜ ተመሳሳይ ፊት ።

Leave a Reply