Soccer Ethiopia

​ጳውሎስ ጌታቸው የባህርዳር ከተማ አሰልጣኝ ሆነው ተሹመዋል

Share

ባህርዳር ከተማ ጳውሎስ ጌታቸውን ቀጣዩ የክለቡ አሰልጣኘ አድርጎ መሾሙ ታውቋል፡፡

በከፍተኛ ሊጉ በተለይ በመጀመሪያው ዙር ጥሩ ጉዞ አድርጎ የነበረውና ወደ ፕሪምየር ሊጉ ለማደግ ሲፎካከር የነበረው ባህርዳር ከተማ በሁለተኛው ዙር ከነበረበት የወጥነት ችግር ለመውጣት እና በቀጣይ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ለማደግ ዋና አሰልጣኙን ጌታሁን ገ/ጊዮርጊስ አሰናብቶ በዝውውሩ ከበርካታ ክለቦች ጋር ስሙ ሲያያዝ የነበረው  ጳውሎስ ጌታቸውን መቅጠሩን አስታውቋል።

የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና እና ሱሉልታ ከተማ አሰልጣኝ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በከፍተኘው ሊግ በሀዲያ ሆሳዕና ጥሩ ቡድን የሰራውና ወደፕሪምየር ሊግ ለማለፍ እስከ መጨረሻው የመቐለ ከተማ የመለያ ጨዋታ ድረስ መድረስ ችሎ ነበር፡፡

1 Comment

Leave a comment

ሶከር ኢትዮጵያ

ሶከር ኢትዮጵያ በ ‘አብርሀም ገ/ማርያም የማስታወቂያ ድርጅት’ ስር የሚሰራ ድረገፅ ሲሆን በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ በሚያተኩሩ ዜናዎች፣ ቁጥራዊ መረጃዎች፣ ታሪኮች፣ ጥልቅ ዘገባዎች፣ አስተያየቶች እና ትንታኔዎች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

ዘርፍ

ማኅደር

top