​ዋልያዎቹ የቻን ዝግጅታቸውን ሀሙስ ይጀምራሉ

በአፍሪካ ሀገራት ሻምፒዮና (ቻን) ሁለተኛ ዙር ማጣርያ የቡሩንዲ እና ሱዳን አሸናፊን የሚገጥመው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሐሙስ በአዳማ ከተማ ዝግጅት እንደሚጀምር ታውቋል፡፡

በመጀመርያው ማጣርያ ጅቡቲን ከሜዳዋ ውጪ 5-1 ካሸነፈች በኋላ በመልሱ ጨዋታ ጅቡቲ እንደማትጫወት በማሳወቋ በፎርፌ ወደ ተከታዩ ዙር ያለፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ተጫዋቾቻቸውን በነገው እለት አዳማ ላይ በሆቴል እንዲሰባሰቡ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን ከሐሙስ ጀምሮ ደግሞ ልምምድ የሚጀምር ይሆናል፡፡

አሰልጣኝ አሸናፊ ለጅቡቲው ጨዋታ ዝግጅት የመረጧቸውን ተጫዋቾች ሙሉ በሙሉ በዚህም ዝግጅት የሚጠቀሙባቸው ሲሆን በጨዋታው ላይ ያልተሰለፉት የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋቾች ጥሪ ተደርጎላቸዋል፡፡ ምንይሉ ወንድሙ ደግሞ በጉዳት ከስብስቡ ውጪ የሆነ ተጫዋች ነው፡፡

ኢትዮጵያ በሁለተኛው ዙር የመጀመርያ ጨዋታዋን ከነሀሴ 5-7 በሜዳዋ ስታደርግ ሁለተኛውን ጨዋታ ከሜዳዋ ውጪ ከ15 ቀናት በኋላ የምታደርግ ይሆናል፡፡ የኢትዮጵያ ቀጣይ ተጋጣሚ የሆኑት ሱዳን እና ቡሩንዲ በመጀመርያ ጨዋታቸው ያለ ግብ ሲለያዩ የመልሱ ጨዋታቸውን በሳምንቱ መጨረሻ የሚያደርጉ ይሆናል፡፡

የብሔራዊ ቡድኑ ስብስብ

ግብ ጠባቂዎች

ጀማል ጣሰው (ድሬዳዋ ከተማ) ፣ ሳምሶን አሰፋ (ድሬዳዋ ከተማ) ፣ ለአለም ብርሃኑ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)

ተከላካዮች

አብዱልከሪም መሃመድ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ አስቻለው ታመነ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ሳላዲን በርጊቾ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ አንተነህ ተስፋዬ (ድሬዳዋ ከተማ) ፣ ሙጂብ ቃሲም (አዳማ ከተማ) ፣ ተስፋዬ በቀለ (አዳማ ከተማ) ፣ ደስታ ዮሀንስ (ሀዋሳ ከተማ) ፣ አምሳሉ ጥላሁን (ፋሲል ከተማ)

አማካዮች

ናትናኤል ዘለቀ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ በኃይሉ አሰፋ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ምንተስኖት አዳነ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ሽመክት ጉግሳ (ደደቢት) ፣ ሙሉአለም መስፍን (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ጋዲሳ መብራቴ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ታፈሰ ሰለሞን (ሀዋሳ ከተማ) ፣ ብሩክ ቃልቦሬ (ወልዲያ)

አጥቂዎች

ጌታነህ ከበደ (ደደቢት) ፣ አዲስ ግደይ (ሲዳማ ቡና) ፣ አብዱልራህማን ሙባረክ (ፋሲል ከተማ) ፣ አሜ መሀመድ (ጅማ አባ ቡና) ፣ ሳላዲን ሰኢድ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *