​ገብረመድህን ኃይሌ በይፋ የጅማ ከተማ አሰልጣኝ ሆነዋል

የፕሪምየር ሊጉ አዲስ ክለብ ጅማ ከተማ አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌን በይፋ የክለቡ አሰልጣኝ አድርጎ ቀጥሯል፡፡

ጅማ ከተማ የተጠናቀውን የውድድር ዘመን በአሰልጣኝ መኮንን ገብረዮሀንስ እየተመራ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ማደግ የቻለ ሲሆን አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ለመሾም መወሰኑ ከሳምንት በፊት ጀምሮ ሲወራ ቆይቶ ነበር፡፡ ሆኖም ክለቡ እስካሁን በይፋ ማስፈረሙን ማረጋገጫ ሳይሰጥ ቆይቶ በመጨረሻም ገብረመድህን ኃይሌን ቀጣዩ የጅማ ከተማ አድርጎ በይፋ ሾሟል፡፡

አሰልጣኝ ገብረመድህን ከጅማ ጋር የ1 አመት ኮንትራት የተፈራረሙ ሲሆን ረዳታቸውን በቀጣዮቹ ቀናት ለክለቡ ያሳውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ አጥቂ በአሰልጣኝነት ዘመናቸው በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ክለቦች ከ1990ዎቹ መጀመርያ አንስቶ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ ትራንስ ኢትዮጵያ ፣ ባንኮች (ንግድ ባንክ) ፣ ኢትዮጵያ መድን ፣ ኢትዮጵያ ቡና ፣ ደደቢት ፣ መከላከያ እና ጅማ አባ ቡና እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን አሰልጥነዋል፡፡ በውድድር አመቱ አጋማሽ ወደ ጅማ አባ ቡና አምርተው ክለቡ መሻሻል እንዲያሳይ ቢረዱትም ክለቡን ከመውረድ ሳይታደጉት ቀርተዋል፡፡

3 Comments

  1. OMG!! ይህንን ፅሁፍ ያቀረብክልን ዳንኤል መስፍን በጣም ያሳዝናል የጅማ አባ ቡና ከሙስናና ከውጤት ማስቀየር ጋር በተያያዘ ጉዳይ ያቀረበው ክስ ውጤቱ በፌዴሬሽኑ በኩል በይፋ ሳይገለጽ ከጋዜጠኝነት ስነምግባር ውጪ ”አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ በውድድር አመቱ አጋማሽ ወደ ጅማ አባ ቡና አምርተው ክለቡ መሻሻል እንዲያሳይ ቢረዱትም ክለቡን ከመውረድ ሳይታደጉት ቀርተዋል” የሚል ወሬ ለህዝብ ማቅረብህ ለመሆኑ ማስረጃህ ምንድነው??ማስረጃህ ፌዴሬሽኑ ከሆነም የሙያህ ስነምግባር ስለሚያስገድድህ ለምን የፍትህ ያለ እያለ እያዘነ ለሚገኘው ህዝብ ውሳኔውን በይፋ አትገልጽም ??

Leave a Reply