የኢትዮጵያ ዋንጫ ፡ ወላይታ ድቻ እና ሀዋሳ ከነማ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቀሉ

የኢትዮጵያ ዋንጫ (ጥሎ ማለፍ) ሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ዛሬ ሲቀጥሉ ሀዋሳ ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወደ ግማሽ ፍፃሜ አልፈዋል፡፡

በ9፡00 ኤሌክትሪክን የገጠመው ወላይታ ድቻ 1-0 አሸንፏል፡፡ የወላይታ ድቻን የድል ግብ አላዛር ፋሲካ በ68ኛው ደቂቃ በሚታወቅበበት የግንባር ኳስ ከመረብ አሳርፏል፡፡

በ11፡00 ኢትዮጵያ ቡናን የገጠመው ሀዋሳ ከነማ 2-1 አሸንፏል፡፡ ኢትዮጵያ ቡና ቢንያም አሰፋ ባስቆጠረው ግብ 1-0 ሲመራ ቢቆይም በ62ኛው ደቂቃ ታፈሰ ተስፋዬን ተክቶ ወደ ሜዳ የገባው ተመስገን ተክሌ በ63ኛው እና 73ኛው ደቂቃ ባስቆጠራቸው ግቦች ሀዋሳ ከነማ 2-1 አሸንፎ ወደ ግማሽ ፍፃሜው አልፏል፡፡ ተመስገን ያስቆጠራቸው ሁለት ግቦች የአጥቂውን ክህሎት ያሳዩ ነበሩ፡፡

ሁለቱ የደቡብ ክለቦች የዛሬ ድላቸውን ተከትሎ በግማሽ ፍፃሜው እርስ በእርስ ይፋለማሉ፡፡ ከ2000 በኋላም አንድ የደቡብ ክለብ ለኢትዮጵያ ዋንጫ ፍፃሜ መድረሱን አረጋግጧል፡፡

ትላንት አርባንጭ ከነማን ያሸነፈው ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሲዳማ ቡናን የረታው መከላከያ ሌሎች የግማሽ ፍፃሜ ተፋላሚዎች ናቸው፡፡

ያጋሩ