​የብሔራዊ ቡድናችን ሰሞነኛ ጉዳዮች

በ2018 በኬንያ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የቻን ውድድር ለማለፍ የመጨረሻ የማጣርያ ጨዋታውን ከሱዳን ጋር የሚያደርገው የኢትዮዽያ ብሔራዊ ቡድን ከውስብስብ ችግሮቹ ጋር በመሆን በአዳማ ከተማ ዝግጅቱን ባልተረጋጋ ሁኔታ ማድረጉን ቀጥሏል፡፡

ከሱዳን ጋር ከነሐሴ 5-7 ባሉት ቀናት የመጀመርያ ጨዋታውን በሀዋሳ ኢንተርናሽናል ስታድየም የሚያደርገው የኢትዮዽያ ብሔራዊ ቡድን ከሐሙስ ጀምሮ አስቀድሞ ከጅቡቲ ጋር የተጠቀመባቸው 18 ተጨዋቾችን ጨምሮ ለቅዱስ ጊዮርጊሶቹ አስቻለው ታመነ ፣ በኃይሉ አሰፋ ፣ ምንተስኖት አዳነ እና ሳላዲን በርጌቾ  ጥሪ ቢያደረጉም ብሔራዊ ቡድኑ በተሟላ ሁኔታ እየተዘጋጀ እንዳልሆነ ለመመልከት ችለናል ።

አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ከቅዱስ ጊዮርጊስ የተመረጡት ተጨዋቾችን ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር እንዲቀላቀሉ ጥሪ ቢያደርጉም የብሔራዊ ቡድኑ የቡድን መሪ የሆኑት አቶ አበበ ገላጋይ ቀድመው ከጅቡቲ ጋር የነበሩት 18 ተጨዋቾች ብቻ በቂ በመሆናቸው ለሌላ ተጨዋች ጥሪ ማድረግ አያስፈልግም በማለት ትዕዛዝ እንደሰጡ ተነግሯል፡፡ በዚህ ውሳኔ ቅር የተሰኙት አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለም በእዚህና በሌሎች ተያያዥነት ባላቸው ችግሮች እንዲሁም ” በስራዬ ጣልቃ እየተገባ የስራ ነፃነት አጥቻለው” በሚል ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር እስከ መስከረም ወር ድረስ ብቻ ቆይተው ከብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝነታቸው ራሳቸውን እንደሚያገሉ መልቀቂያ ማስገባታቸውን ለማወቅ ችለናል።

ብሔራዊ ቡድኑ ከኤሪያ ጋር በገባው ውል መሰረት የቀረበለት ከበዝግጅት ወቅት የሚጠቀሙባቸው አልባሳት ደረጃውን ያልጠበቀ ነው በሚል አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ በራሳቸው ወጪ መግዛታቸውም ታውቋል፡፡

አሰልጣኙ መልቀቂያ ለማስገባት ያበቃቸውን ምክንያት እና አሉ በተባሉ ችግሮች ዙርያ አስተያየታቸውን ለመቀበል ሶከር ኢትዮጵያ ዛሬ በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታድየም ብትገኝም አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ አስተያየት ለመስጠት ፍቃደኛ አለመሆናቸውን ገልፀዋል።  ያም ሆኖ ከአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ሁኔታ መረዳት የሚቻለው በስራቸው ደስተኛ እንዳልሆኑና ምናልባትም የተለየ ነገር ካልተፈጠረ በቀር ባስገቡት የመልቀቂያ ደብዳቤ አቋሟቸው የሚፀኑ ይመስላል ።

በተፈጠረው ችግር ዙርያ የኢትዮዽያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት አቶ ጁነይዲ ባሻ አስተያየታቸውን የሰጡ ሲሆን ችግሩ እንዳለ አምነው በፍጥነት ለተፈጠረው ችግር መፍትሔ ለመስጠት እየሞከሩ እንደሆነ ተናግረዋል። የክልል ሻምፒዮና መክፈቻ ላይ ለመገኘት ወልድያ የነበሩት አቶ ጁነይዲ ከወልድያ እንደተመለሱ ነገ ወደ አዳማ ከተማ በማቅናት ከአሰልጣኞቹ እና ከተጨዋቾቹ ጋር በመነጋገር የቡድኑን መንፈስ ለመጠበቅ ፣ ለማነቃቃት እና አሉ የተባሉ ችግሮችን ለመፍታት ጥረት እንደሚያደርጉ አሰልጣኝ አሸናፊ ወጪ ካወጡም ወጪው በፌዴሬሽኑ እንደሚወራረድ ለሶከር ኢትዮዽያ ተናግረዋል።

ለብሔራዊ ቡድኑ የተሰጠው ግምት እና ትኩረት አናሳ እንደሆነ ብሔራዊ ቡድኑ በሚያደርገው ዝግጅት ላይ መታዘብ ችለናል። ስለሆነም ብሔራዊ ቡድኑ የሚመለከታቸው አካላት አስፈላጊውን ነገር ሁሉ ሊያደርጉለት ይገባል መልክታችን ነው።

5 Comments

 1. የሚገርም ነው! እኔ እምለው የኛ EFF አለቃው ሁሉም ነው እንዴ? አቶ አበበ ገላጋይ ለዚህ አመለካከታቸው በቶሎ ገላጋይ ሊፈልጉለት ይገባል፡፡ ካልሆነ በሚደርሰው የእግር ኳሱ ውድቀት የስፖርት ቤተሰቡ በሚወስዳቸው እርምጃዎች እንዳይፀፀቱ፡፡ ቆይ በ104ሚሊዮን ህዝብ በሚወከል ቡድን ላይ አንድ የኢለመንተሪ ት/ቤት ተማሪ ሊወስነው የማይደፍረውን ውሳኔ ማሳለፍ ከጤነኛ አዕምሮ የመነጨ አይመስለኝም፡፡ ስለዚህ አቶ አበበን ወደ አማኑኤል ሆስፒታል ብሔራዊ ቡድኑን ያለ እንከን ወደ ቻን መላክ ያስፈልጋል፡፡

 2. አቶ አበበ ገላጋይ ወደው አይደለም እንደዚህ ሊሉ የቻሉት. ከቅዱስ ጊዮርጊስም ተመረጡ ከአዲስ አበባ ከተማ በትላልቅ ቡድኖች ይሸነፋሉ አነስ ያሉትን ያሸንፋሉ፡፡ ለሽንፈት ከቅዱስ ጊዮርጊስም ተመረጠ ከሌላ ልዩነት የለውም፡፡ ሀገር ለመጎብኘት ስለሆነ የሚሄዱት ሁሉም በየተራ እየሄዱ ቢጎበኙ ምናለበት( ቅዱስ ጊዮርጊሶች በክለብ ስለሚሄዱ)፡፡ ስለዚህ ሰውዬው ብዙም አላጠፉም፡፡

 3. የአንድ ሀገር ብሒራዊ ቡድን ማለት:- በኢንተርናሽናል መድረክ የሀገሩን መልካም ገፅታ የሚያስተዋዉቅ ትልቁ ስዕል በአደባባይ የሚሰቅል በከፍተኛ ባለሙያዎቾ የሚመራ በህብረተሰቡም ሆነ በከፍተኛ የመንግስት አመራሮችና ፕሮፌሽናል ባለሙያዎች የሚታገዝና ክብር የሚሰጠዉ የዓለማችን ተወዳጅ ስፖርት ነዉ..

  …ይህን ወደ ሀገራችን ስንመነዝረዉ ..ኢትዮጵያችን በአትሌቲክሱ ዘርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስመ ገናና ብትሆንም እጅግ አብልጫዉ ህብረተሰብ ግን ለእግር ኳሱ ያለው ጥልቅ ስሜት ሚዛን የሚደፋ ነዉ…

  ..ይህም ሆኖ የህዝቡ ጥልቅ ስሜትና የብሔራዊ ቡድናችን ዉጤት የሚመጣጠን ባይሆንም ክብሩና ግርማ ሞገሱ/IDENTIY/.. ግን መቼም ቢሆን ሊወርድ አይገባዉም…በመሆኑም በአሁኑ ወቅት የዋልያዎቹ አለቃ በሚያወጡት ዕቅድ መሰረት የሚመለከተዉ ክፍል አስፈላጊዉን ድጋፍ ሊያደርግላቸዉ ይገባል…

  …ሙያን ለባለሙያ በመስጠት ብሎም ፍፁም የሥራ ነፃነት ያለገደብ በመልቀቅ “ሰፍረዉ የሰጡትን ሰፍረዉ መረከብ ይበጃል”…ዳሩ ግን ለ CAF..የቻን ዉድድር ወሳኝ ጫፍ ላይ በተደረሰበት ወቅት ይህን መሰል ዉዝግብ መስማት እንደኔ የህዝቡን የስሜት ጡዘት ልብ አለማለትን ወይም በቸልታ ከማስተናገድ የመነጨ የግዴለሽነት አሰራሮችን የሚያመላክት ይሆናል ብዬ አስባለሁ…

  …ደግሞስ ፌዴሬሽኑ አሰልጣኙን ሲቀጥር ያስቀመጣቸዉን ራዕይ ያሰፈፅምልኛል ብሎ አይደለምን..? ከሆነ ሥጋ ሰጥቶ ቢላዋ መከልከል እንዳይመስል ሊታሰብበት ይገባል…የምንሰማቸዉ አሉታዊ ነገሮች ወደ መልካምነት ተለዉጠዉ የብሔራዊ ቡድናችን ሠፈር የሰላም አየር ጎብኝቶት ወሳኙን ዉድድር በዉጤት ይቋጩት ዘንድ ተመኜሁ..

 4. የቤታችሁን አመል እዛው ተውትና እንደ ሀገር አስቡ!!!

 5. Abebe Gelagay is a very arrogant, shameful and ignorant person and one who is the enemy of foot ball. He should be fired 1000 km away from the foot ball federation. Who the hell does he think he is interfering in the what is the sole duty of the coach in the manner that he did. It is a shameful act and the federation should be ashamed of this complete lack of professional ethics. I wish the national team is disbanded until a new EFF executive is elected. It is a total shame. Coach Ashenafi should resign after the CHAN qualification and give official press conference and make every thing public.

Leave a Reply