የኮፓ ኮካ ኮላ ከ15 አመት በታች ታዳጊዎች ሀገር አቀፍ ውድድር ከነሀሴ 13 ጀምሮ በኢትዮ ሶማሌ ጅግጅጋ ይደረጋል፡፡
ውድድሩ ከሚያዝያ ወር ጀምሮ በክልሎች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች የውስጥ ውድድር (ግራስሩት) የተደረገ ሲሆን በውስጥ ውድድሩ የተሻለ እንቅስቃሴ ያሳዩ ታዳጊዎች ዞናቸውን ወክለው በክልል አቀፍ ውድድር ላይ ተሳትፈዋል፡፡ ከክልል አቀፉ ውድድር ላይ የተውጣጡ ታዳጊዎች ደግሞ ክልላቸውን/የከተማ አስተዳደራቸውን ወክለው ጅግጅጋ ላይ ወደሚደረገው የሚያመሩ ይሆናል፡፡
ጅግጅጋ ለውድድሩ መሰናዶ ዝግጅቷን እያጠናቀቀች ሲሆን ሁለት የመጫወቻ ሜዳዎች ተዘጋጅተዋል፡፡ ከነዚህም መካከል አንደኛው ሜዳ በቅርብ ተሰርቶ የተጠናቀቀ እና የሰው ሰራሽ ሳር የተነጠፈለት ነው፡፡
ኮፓኮካ ኮላ ዘንድሮ ለ3ኛ አመት የሚካሄድ ሲሆን የአምናው ተመሳሳይ ውድድር በቢሾፍቱ ተዘጋጅቶ በወንዶች ደቡብ ፣ በሴቶች ኦሮሚያ አሸናፊ መሆናቸው ይታወሳል፡፡ በውድድሩ ላይ ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ ያሳዩ ተጫዋቾች ወደ ኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ እና ጥሩነሽ ዲባባ ስፖርት አካዳሚ የሚገቡ ይሆናል፡፡
ፎቶ – ከላይ የወንዶች የአምና አሸናፊ ደቡብ ክልል ፣ ከታች የሴቶች የአምና አሸናፊ ኦሮሚያ ክልል