ከፍተኛ ሊግ | አዲስ አበባ ከተማ 12 አዳዲስ ተጫዋቾች አስፈርሟል

በኢትዮዽያ ፕሪምየር ሊግ ለመጀመርያ ጊዜ በተሳተፈበት አመት ተመልሶ የወረደው አዲስ አበባ ከተማ ወደ ሊጉ ለመመለስ እንዲረዳው በተጫዋቾች ዝውውር ላይ በስፋት እየተሳተፈ ይገኛል፡፡

በአሰልጣኝ አስራት አባተ የሚመራው አዲስ አበባ ከተማ በቡድኑ ከሚገኙ ተጫዋቾች መካከል ቀሪ ኮንትራት ያላቸው 15 ተጫዋቾች እንደሚቀጥሉ የታወቀ ሲሆን እስካሁን ባደረገው እንቅስቃሴ አንድ ደርዘን ተጫዋቾች አስፈርሟል፡፡

በግብ ጠባቂ ስፍራ ላይ ሐፍቶም ቢሰጠኝ (ሽረ እንዳስላሴ) እና ዋኬኒ አዱኛ (ቡታጅራ ከተማ)ን ሲያስፈርም በተከላካይ መስመር ላይ ፋሲል ጌታቸው (ባህርዳር ከተማ) ፣ ተስፋዬ ሀላላ (ኢትዮዽያ ውሃ ስራ) ፣ ማታይ ሉል (ፌደራል ፖሊስ) እና ሚሊዮን ሰለሞን (ሀንበሪቾ) የግሉ ማድረግ ችሏል፡፡

ሚልዮን ሰለሞን

በአማካይ ስፍራ ላይ ኄኖክ አንጃ (ለገጣፎ ለገዳዲ) ፣ ፀጋዬ ከፍያለው (ቡራዩ ከተማ) ፣ ጌታነህ ሙሉነህ (ለገጣፎ ለገዳዲ) ፣ ሙሴ እንዳለ (ሚዛን አማን) ፣ ገናናው ረጋሳ (ባህርዳር ከተማ) እና እንዳለማው ታደሰ (ለገጣፎ ለገዳዲ) ለክለቡ ፊርማቸውን የአጥቂ ስፍራ ተጨዋቾችን ለማስፈረም እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

ፎቶ ከላይ :- ማታይ ሉል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *