የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና 8ኛ ቀን ውሎ
የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና የምድብ ጨዋታ እሁድ ሲጠናቀቅ ወደ 2ኛ ዙር ያለፉ ክለቦች ሙሉ ለሙሉ ታውቀዋል፡፡
ምድብ 1
በ8:00 በሙሐመድ ሁሴን አሊ አል–አሙዲ ስታድየም በሽረ እንዳስላሴ ቢ እና ኢተያ ከተማ ጨዋታ በተደረገው ጨዋታ ሽረ 1-0 በማሸነፍ ወደ 2ኛ ዙር ማለፉን አረጋግጧል፡፡ በፈጣን እንቅስቃሴ በጀመረው ጨዋታ በ3ኛው ደቂቃ ከቀኝ መስመር የተላከውን ኳስ አምበሉ ሸሻይ ኪዳነ አስቆጥሮ ሽረን መሪ አድርጓል።
የጨዋታው ድባብ ቀስ በቀስ አላስፈላጊ መጎሻሸሞች እና ኃይል የቀላቀለበት ጨዋታ ይዘት እየያዘ የመጣ ሆኗል። የሽረ የአሰልጣኞች ስታፍ እና ቡድን መሪ በተደጋጋሚ ከዳኞች ጋር እሰጣ ገባ ውስጥ ሲገቡ የተስተዋለ ሲሆን በ28ኛው ደቂቃ የሽረ ቡድን መሪ ኤፍሬም ሐዱሽ በእለቱ የመሀል ዳኛ በቀይ ካርድ ከሜዳ እንዲወጣ ተደርጓል።
ከእረፍት መልስ በሁለቱም በኩል ተመጣጣኝ እና ፈጣን የሚባል እንቅስቃሴ የተስተዋለ ሲሆን ኢተያ የሙከራ የበላይነት ወስደዋል፡፡ በ70ኛው ደቂቃ ጣሒር ሰይፍ ከሽረ ግብ ጠባቂ የተመለሰውን ኳስ አግኝቶ በጎሉ በላይ የላከው እና በ76ኛው ደቂቃ ሁለት የሽረ ተከላካዮች አታሎ በተመሳሳይ በጎሉ አናት የላከው ኳስ በኢተያ በኩል ለግብ የቀረቡ አጋጣሚዎች ነበሩ። በሁለተኛው አጋማሽ እንደመጀመሪያው አጋማሽ ባይደጋግምም መጎሻሸሞች የተስተዋሉ ሲሆን በ90ኛው ደቂቃ የኢተያው አህመድ ሁሴን በሽሬ ግብ ጠባቂ ላይ በፈፀመው ጥፋትት የቀይ ካርድ ሰለባ ሆኗል። ጨዋታውም በሽረ 1-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
በዚሁ ምድብ በተመሳሳይ ሰአት በተካሄደ ሌላ ጨዋታ ያሶ ከተማ ሾኔን 3-1 ቢያሸንፍም ተያይዘው ከምድባቸው ተሰናብተዋል፡፡
ምድብ 2
ከዚህ ምድብ ድሬዳዋ ኮተን ከምድቡ አስቀድሞ ማለፉን በማረጋገጡ ሌላኛውን አላፊ ቡድን የሚለዩ ጨዋታዎች ተደርገዋል፡፡ መልካ ቆሌ ላይ መርካቶ አካባቢ ቤንችማጂ ፖሊሰን 2-0 በመርታት ወደ 2ኛው ዙር ሲያልፍ ቡሬ ከተማ ከመተከል ፖሊስ 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ጨዋታቸውን አጠናቀው ተያይዘው ከምድቡ ተሰናባች ሆነዋል፡፡
ወደ 2ኛዙር ያለፉ ክለቦች
ምድብ 1 – የጁ ፍሬ ወልዲያ ፣ ሽረ እንዳስላሴ ቢ
ምድብ 2 – ድሬዳዋ ኮተን ፣ መርካቶ አካባቢ
ምድብ 3 – ናኖ ሁርቡ ፣ አሳሳ ከተማ
ምድብ 4 – ሰንዳፋ በኬ ፣ ነስር ክለብ
ምድብ 5 – መርሳ ከተማ ፣ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ
ምድብ 6 – አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ፣ ገንደውሀ ከተማ
ምድብ 7 – ጉለሌ ክፍለከተማ ፣ ገንፈል ውቅሮ
ምድብ 8 – ሺንሺቾ ከተማ ፣ ጫንጮ ከተማ
About Post Author
Mohammed
ተዛማጅ ፅሁፎች
የሉሲዎቹ ዋና አሰልጣኝ ተጫዋቾችን ጠርተዋል
በዩጋንዳ ለሚደረገው የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለ23 ተጫዋቾችን ጥሪ አድርሷል፡፡ በዩጋንዳ ከግንቦት 24 ጀምሮ ለተከታታይ አስር ቀናት ለሚደረገው...
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ውድድር ተራዘመ
የሴቶች ፕሪምየር ሊግ የሁለተኛው ዙር ውድድር የሚጀመርበት ቀን ተገፍቷል፡፡ የ2014 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያው ዙር ጨዋታዎች በሀዋሳ ጅምራቸውን አድርገው...
የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ ተራዘመ
በዩጋንዳ አስተናጋጅነት የሚዘጋጀው የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ የቀን ማሻሻያ ተደርጎበታል፡፡ ሉሲዎቹን ተሳታፊ የሚያደርገው የዘንድሮው የሴካፋ የሴቶች ዋንጫ በዩጋንዳ አስተናጋጅነት እንደሚደረግ ይጠበቃል፡፡...
“በእያንዳንዱ ጨዋታ የሚሰጠኝን ዕድል መጠቀም ላይ ነው እያተኮርኩ ያለሁት” ዳግም ተፈራ
በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ እየታዩ ካሉ ጥሩ ግብ ጠባቂዎች መካከል አንዱ ከሆነው ወጣት ጋር ቆይታ አድርገናል። የ2014 የቤትኪንግ የኢትዮጵያ...
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ተካሂዷል
ከረፋድ አንስቶ ካዛንቺስ በሚገኘው የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን መሰብሰቢያ አዳራሽ ሲካሄድ የዋለው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ...
ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ የ17ኛ ሳምንት የዛሬ ጨዋታዎች ውሎ
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ የ17ኛ ሳምንት የመጀመርያ ቀን ጨዋታዎች ዛሬ ሲካሄዱ ሀዋሳ ከተማ ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሀዲያ...
Average Rating