በ2009 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጨረሻ ሳምንት በኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ሀዋሳ ከነማ መካከል ከተደረገው ጨዋታ ጋር ተያይዞ የሀዋሳ ከተማ ‘የክለቤ ተጫዋች ኤፍሬም ዘካርያስ የጨዋታን ውጤት ያለአግባብ ለማግኘት ከኤሌክትሪክ ጋር ሲደራደር አግኝቼዋለሁ’ በማለት ተጫዋቹ ላይ ቅጣት ማስተላለፉን ተከትሎ ጅማ አባ ቡና ጉዳዩ እንዲጣራለት ለፌደሬሽኑ በደብዳቤ ማሳወቁ የሚታወስ ነው፡፡ ይህንን ተከትሎም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ጉዳዩን ለማጣራት ኮሚቴ አቋቁሞ ሲንቀሳቀስ መቆየቱን መግለጹ የሚታወስ ሲሆን ጅማ አባ ቡናም የምርመራው ውጤት እና ውሳኔ በቶሎ እንዲገለፅ ደብዳቤ ማስገባቱ ይታወሳል፡፡
የጉዳዩን አሳሳቢነት ተከትሎ የተለያዩ የስፖርት ቤተሰቦች ውሳኔውን ለመስማት የጓጉ ሲሆን ፌደሬሽኑም በጉዳዩ ላይ ያደረገውን ምርመራ ውጤት እና ያሳለፈውን ውሳኔ በነገው እለት በኢንተር ኮንትኔንታል አዲስ ሆቴል ከቀኑ በ10:00 ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡