በክልል ክለቦች ሻምፒዮና ወደ ግማሽ ፍፃሜ ያለፉት ክለቦች ታውቀዋል
የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና በወልዲያ መደረጉን ቀጥሎ ወደ አንደኛ ሊግ ማደጋቸውን ያረጋገጡ 8 ክለቦች ባደረጓቸው የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ወደ ግማሽ ፍጻሜ ያለፉ ክለቦች ታውቀዋል፡፡
ረፋድ 3:00 ላይ በተካሄደው የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ እና ሺንሺቾ ከተማ ጨዋታ አቃቂ 1-0 በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍጻሜው ተሸጋግሯል፡፡ ቀጥሎ በተደረገው ጨዋታም ሌላው የአዲስ አበባ ክለብ ጉለሌ ክፍለከተማ ከ መርሳ ከተማ ጋር በመደበኛው የጨዋታ ክፍለጊዜ 2-2 አቻ ተለያይተው በመለያ ምቶች ጉለሌ 4-2 በማሸነፍ ሁለተኛው የግማሽ ፍጻሜ ተፋላሚ ሆኗል፡፡
በከሰአት መርሃ ግብር በተደረገው የድሬዳዋ ኮተን እና ሰንዳፋ በኬ ጨዋታ ሰንዳፋ 2-1 አሸንፏል፡፡ በመጀመሪያው አጋማሽ የሰንዳፋ በኬ ማራኪ የጨዋታ እንቅስቃሴ እና የግብ ሙከራ የበላይነት ቢስተዋልበትም ያገኟቸውን የግብ እድሎች ወደ ግብ መቀየር ሳይችሉ ቀርተዋል። በዚህም ያለምንም ግብ ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል።
ከእረፍት መልስ ተመጣጣኝ እንቅስቃሴ የተስተዋለ ሲሆን በ65ኛው ደቂቃ ሰንዳፋዎች በማራኪ ቅብብል ይዘው የገቡትን ኳስ ፋሲል ደስታ በጥሩ ሁኔታ አስቆጥሮ ሰንዳፋ መሪ አድርጓል። በ69ኛው ደቂቃ አሰልጣኛቸው ከዳኛ ጋር በፈጠረው አለመግባባት ከሜዳ እንዲወጣ የተደረገባቸው ኮተኖች ግብ ከተቆጠረባቸው በኋላ ተጭነው በመጫወት በ75ኛው ደቂቃ ሳሙኤል ዘሪሁን አስቆጥሮ ወደ ጨዋታው ተመልሰዋል፡፡
በጥሩ የመሸናነፍ ስሜት በቀጠለው ጨዋታ በ89ኛው ደቂቃ ሰንዳፋዎች ያገኙት የማእዘን ምት ተሻምቶ ግብ ጠባቂው ሲመልሰው ባቅራቢያው የነበረው ዮሀንስ ጌታቸው አስቆጥሮ ሰንዳፋ 2-1 እንዲያሸንፍ ረድቶታል፡፡ በ90ኛው ደቂቃ በተጫዋቾች መካከል በተፈጠረ ግጭት ከድሬዳዋ ኮተን አብዱ አህመድ እንዲሁም ከሰንዳፋ በኬ ደረጄ አበራ በቀይ ከሜዳ ተወግደዋል።
የእለቱ የመጨረሻ መርሀግብር ወልድያ የጁ ፍሬን ከናኖ ሆርቡ ያገናኘ ሲሆን ናኖ ሁርቡ 2-0 ማሸነፍ ችሏል፡፡ በመጀመርያው አጋማሽ ሁለቱም ወደ ግብ በተደጋጋሚ ቢደርሱም ግብ ሳይስተናገድ ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል።
ከእረፍት መልስ በ52ኛው ደቂቃ ከማዕዘን ምት ተሻምቶ ሲመለስ በፈጣን መልሶ ማጥቃት ይዘውት የመጡትን ኳስ ምንተስኖት አብሹ አስቆጥሮ ናኖ ሁሩቡን መሪ አድርጓል። ወልድያዎች ከግቧ መቆጠር በኋላ ብልጫ ተጭነው ቢጫወቱም በ67ኛው ደቂቃ ኤርሚያስ ጥበበ በጭንቅላት ገጭቶ ባስቆጠረው ጎል የናኖ ሁርቡን መሪነት አስተማማኝ አድርጎታል፡፡ የጁ ፍሬዎች ቀሪዎቹን ደቂቃዎች ብልጫ ወስደው ተጭነው መጫወት ቢችሉም ጠንካራ የነበረው የናኖ ተከላካይ አልፎ ግብ ለማስቆጠር ተቸግረዋል።ጨዋታውም በናኖ ሁሩቡ 2ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል።
About Post Author
Mohammed
ተዛማጅ ፅሁፎች
የሉሲዎቹ ዋና አሰልጣኝ ተጫዋቾችን ጠርተዋል
በዩጋንዳ ለሚደረገው የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለ23 ተጫዋቾችን ጥሪ አድርሷል፡፡ በዩጋንዳ ከግንቦት 24 ጀምሮ ለተከታታይ አስር ቀናት ለሚደረገው...
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ውድድር ተራዘመ
የሴቶች ፕሪምየር ሊግ የሁለተኛው ዙር ውድድር የሚጀመርበት ቀን ተገፍቷል፡፡ የ2014 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያው ዙር ጨዋታዎች በሀዋሳ ጅምራቸውን አድርገው...
የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ ተራዘመ
በዩጋንዳ አስተናጋጅነት የሚዘጋጀው የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ የቀን ማሻሻያ ተደርጎበታል፡፡ ሉሲዎቹን ተሳታፊ የሚያደርገው የዘንድሮው የሴካፋ የሴቶች ዋንጫ በዩጋንዳ አስተናጋጅነት እንደሚደረግ ይጠበቃል፡፡...
“በእያንዳንዱ ጨዋታ የሚሰጠኝን ዕድል መጠቀም ላይ ነው እያተኮርኩ ያለሁት” ዳግም ተፈራ
በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ እየታዩ ካሉ ጥሩ ግብ ጠባቂዎች መካከል አንዱ ከሆነው ወጣት ጋር ቆይታ አድርገናል። የ2014 የቤትኪንግ የኢትዮጵያ...
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ተካሂዷል
ከረፋድ አንስቶ ካዛንቺስ በሚገኘው የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን መሰብሰቢያ አዳራሽ ሲካሄድ የዋለው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ...
ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ የ17ኛ ሳምንት የዛሬ ጨዋታዎች ውሎ
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ የ17ኛ ሳምንት የመጀመርያ ቀን ጨዋታዎች ዛሬ ሲካሄዱ ሀዋሳ ከተማ ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሀዲያ...
Average Rating