ኢትዮጵያ 1-1 ሱዳን፡ የአሰልጣኞች አስተያየት

ኢትዮጵያ እና ሱዳን በቻን ማጣሪያ ሀዋሳ ላይ ባደረጉት ጨዋታ 1-1 ተለያይተዋል፡፡ ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላም የሁለቱ ሃገራት አሰልጣኞች ለጋዜጠኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

“ቡድናችን ጥሩ አልነበረም” የኢትዮጵያ አሰልጠኝ አሸናፊ በቀለ

ስለጨዋታው

“ጨዋታችን እንደጠበቅኩት ጥሩ አይደለም፡፡ ከዚህ በፊት ከተጫወትነው ጨዋታ የወረደ ነው፡፡ በሶስት የተከላካይ አማካይ አይደለም የተጠቀምነው (የምንተስኖት እና ብሩክ ተቀይረው ከገቡ በኃላ)፡፡ ምንተስኖት ተደራቢ አጥቂ ሆኖ ነው እንዲጫወት ነው፡፡ ብሩክ ቃልቦሬ መስመር ላይ ሆኖ እንዲጫወት ነው ያደረግነው፡፡ በአራት ተከላካይ እና በአራት የአማካይ ተከላካይ አልተጫወትንም፡፡”

“ዛሬ ቡድኑ ጥሩ አይደለም፡፡ ከዚህ በፊት ካደረግናቸው ተከታታይ ጨዋታዎች ዛሬ የህዝቡም ተፅዕኖም ይሆን ያልጠበቅናቸው ነገሮች ይገጥማሉ፡፡ ዛሬ በልጆቼ እንቅስቃሴ ብዙም ደስተኛ አይደለሁም፡፡ ደጋፊያችንም የሚጠብቀውን ያህል አልነበረም የተጫወትነው፡፡”

የሁለተኛ 45 የሱዳን የተሻለ መንቀሳቀስ

“እኛ ነን አጋጣሚውን የፈጠርንለት፡፡ እነሱም ረጅም ኳስ እኛም ረጅም ኳስ ተመሳሳይ ሆነ፡፡ ተክለሰውነት ይህንን አልፈቀደልንም፡፡ የልጆቻችን እና ስብስባችን እንደምታውቋቸው ኳስ የሚችሉ ልጆች ናቸው፡፡ የፈለግነውን አይደለም የተጫወትነው፡፡ የገቡት ልጆች እራሱ ለረጅም ኳስ የሚሆኑ አይደሉም፡፡”

“ይህንን ውጤት ማግኘታችን ይገባናል” የሱዳን አሰልጣኝ መሃመድ አብደላ አህመድ

ስለጨዋታው

“በሁለተኛው አጋማሽ የተሻለ እንቅስቃሴ ነበር፡፡ በሁለተኛው አጋማሽ በተሻለ የመጫወት ፍላጎት ነበር፡፡ እኔ እንደማስበው ይህንን ውጤት ማግኘታችን ይገባናል፡፡ ከዚህ የበለጠ ግቦችን ማስቆጠር የምንችልበት እድልም ነበር፡፡ ጥሩ ጨዋታ ተመልካቹ እንደተመለከተ ተስፋ አደርጋለው፡፡”

ስለመልሱ ጨዋታ

“እግርኳስ ነው የምንጫወተው፡፡ ከዚህ በፊት ለማለፍ ተቸግረን ነበር፡፡ አሁን ላይ ማለፍ ነው አላማችን፡፡ በሜዳችን ጥሩ እንጫወታለን ብዬ አስባለው፡፡ ቀላል ጨዋታ እንደማይሆን እጥብቃለው፡፡”

“በአሁኑ ግዜ ከሜዳ ውጨ ጥሩ ልትጫወት ትችላለህ፡፡ ስለዚህም በዚህ ውጤት ላይ አንኩራራም፡፡ አሁንም ፊታችንን ወደ ዝግጅት እናዞራለን፡፡ ብዙ እድሎችን አምክነናል በዚህ ላይ መስራት አለብን፡፡”

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *