ለ20 አመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን 31 ተጫዋቾች ጥሪ ቀረበላቸው

የኢትየጵያ ከ20 አመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ቴዎድሮስ ደስታ ቡድናቸው በ2018 የፈረንሳይ አለም ዋንጫ ማጣርያ ከኬንያ ጋር ለሚያደርጉት ጨዋታ ዝግጅት ለ31 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል።

ለቡድኑ ጥሪ ከተደረገላቸው ተጫዋቾች መካከል በ2016 የጆርዳን የአለም ከ17 አመት በታች ሴቶች ዋንጫ ማጣርያ ላይ ከተካፈለው ቡድን 10 ተጫዋቾች ተካተዋል፡፡ የ17 አመት በታች ቡድኑን በአምበልነት መርታ የነበረችው እመቤት አዲሱ ፣ ካሜሩን ላይ ከሜዳ ውጪ ግብ ያስቆጠረችው ሜላት ደመቀ ፣ በተመሳሳይ ካሜሩን ላይ በአዲስ አበባው የመልስ ጨዋታ ግብ ያስቆጠሩት ትደግ ፍስሀ እና የምስራች ላቀውን ጨምሮ እምወድሽ ይርጋሸዋ ፣ ቅድስት ዘለቀ ፣ ሳምራዊት ኃይሉ ፣ ሴናፍ ዋቁማ ፣ ምርቃት ፈለቀ እና ትመር ጠንክር ካለፈው የ17 አመት በታች ቡድን ውስጥ የተካተቱ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

የተመረጡ ተጫዋቾች ዝርዝር

ግብ ጠባቂ

እምወድሽ ይርጋሸዋ (አዳማ ከተማ) ፣ ትዕግስት አበራ (ሀዋሳ ከተማ) ፣ ቤተልሄም የኑስ (ጌዲኦ ዲላ) ፣ ሰናይት አስራት (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)

ተከላካዮች
አረጋሽ ፀጋዬ (ሃዋሳ ከተማ) ፣ ቅድስት ዘለቀ (ሃዋሳ ከተማ) ፣ ብዙአየሁ ታደሰ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ዮርዳኖስ ጌታነህ (አዳማ ከተማ ) ፣ ሳምራዊት ኃይሉ (መከላከያ) ፣ ቤተልሄም ከፍያለው ( ኢትዮ ኤሌትሪክ) ፣ ገነሜ ወርቁ (ሲዳማ ቡና) ፣ ባንቺአየሁ ታደሰ (አዳማ ከተማ) ፣ መስከረም ኢሳይያስ (አርባምንጭ ከተማ ) ፣ ዘነበች ዘመዱ (ንፋስ ስልክ ላፍቶ)

አማካዮች

እመቤት አዲሱ (መከላከያ) ፣ የምስራች ላቀው (መከላከያ) ፣ ነፃነት መና (ሀዋሳ ከተማ) ፣ ሜላት ደመቀ (አዲስ አበባ ከተማ) ፣ ብሩክታዊት አየለ (መከላከያ) ፣ ጽዮን ፈየራ (ኢትዮ ኤሌትሪክ) ፣ ሳራ ኬዲዮ (አርባምንጭ ከተማ) ፣ ዘይነባ ሰዒድ (ኢትዮ ኤሌትሪክ)

አጥቂዎች
ሴናፍ ዋቁማ (አዳማ ከተማ) ፣ ምርቃት ፈለቀ (ሀዋሳ ከተማ) ፣ ፋሲካ ንጉሴ (ጌዲዮ ዲላ) ፣
ልደት ቶሎአ (አርባምንጭ ከተማ) ፣ ትደግ ፍሰሃ (ደደቢት) ፣ አለምነሽ ገረመው (ኢትዮ ኤሌትሪክ) ፣ ጤናዬ ወመሴ (ኢትዮ ኤሌትሪክ) ፣ ትመር ጠንክር (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ትዝታ ፈጠነ (አርባምንጭ ከተማ)

ቡድኑ በነገው እለት ወደ ድሬዳዋ የሚያቀና ሲሆን በነሃሴ ወር መጨረሻ 25 ተጨዋቾችን ይለያሉ ተብሎ ሲጠበቅ የዋናው አሰልጣኝ ቴዎድሮስ ደስታ ምክትል ሰርካዲስ እውነቱ እንዲሁም የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ ደግሞ ተረፈ ጉደታ ሆነው እንደተመረጡ ታውቋል። የመጀመርያው ጨዋታም መስከረም 7 ድሬዳዋ ላይ የሚካሄድ ይሆናል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *