የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤውን ቅዳሜ ያደርጋል

በኢትዮዽያ እግርኳስ ታሪክ ቀዳሚ የክልል/ከተማ አስተዳደር በመሆን የተቋቋመው የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን የፊታችን ቅዳሜ ነሐሴ 20 ቀን 2009 ከጠዋቱ 02:30 ጀምሮ በኢትዮዽያ ሆቴል የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ አባላት ፣ የክፍለ ከተማው ተወካዮች ፣ ክለቦች ፣ የተለያዩ ማህበራት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ጠቅላላ ጉባኤውን እንደሚያካሂድ ታውቋል፡፡

በጠቅላላ ጉባኤው ላይም የ2009 አመት ሪፖርት ፣ የኦዲት ሪፓርት ፣ በተቋሙ ተፈጠሩ ሰለተባሉት የአሰራር ክፍተቶች እና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች ይነሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *