የዝውውር መስኮቱ ከተከፈተ ጀምሮ ስሙ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ሲያያዝ የቆየው ሳምሶን ጥላሁን በመጨረሻም ለክለቡ ፊርማውን አኑሯል፡፡
ሳምሶን በደሞዝ ምክንያት ከደደቢት ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብተው ከነበሩ ተጫዋቾች መካከል የነበረ ሲሆን በክለቡ የተላለፈበት እገዳን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በመሻሩ ምክንያት መልቀቂያውን በማግኘቱ ለኢትዮጵያ ቡና በሁለት አመታት ኮንትራት ፈርሟል፡፡
በ2006 ቅዱስ ጊዮርጊስን በመልቀቅ ደደቢትን የተቀላቀለው የመሀል አማካዩ ሳምሶን ክለቡን ከተቀላቀሉት ክሪዚስቶም ንታንቢ እና አስራት ቱንጆ እንዲሁም በክለቡ ከሚገኘው ኤልያስ ማሞ ጋር መልካም የአማካይ ክፍል ጥምረት ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡