ኢትዮጵያ ቡና ወንድይፍራው ጌታሁንን አስፈርሞ ሶስት ተጫዋቾች በውሰት ተሰጥቷል

ወንዲፍራው ጌታሁን ኢትዮጵያ ቡናን ለቆ ወደ ሀዋሳ ከተማ የፈረመ ቢሆንም ለኢትዮጵያ ቡና በድጋሚ መፈረሙን ተከትሎ ውዝግብ ውስጥ ገብተው የነበረ ሲሆን አሁን ለኢትዮጵያ ቡና ተወስኖለት ክለቡን በይፋ ተቀላቅሏል፡፡ ሶስት ተጫዋቾች ደግሞ በውሰት ክለቡን ለቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ቡናን ለቆ ለሀዋሳ ከተማ ለመጫወት ተስማምቶ ፊርማውን ለሀዋሳ ከተማ ያኖረው ወንድይፍራው መልቀቂያ ከኢትዮጵያ ቡና አለመውሰዱን ተከትሎ ኢትዮጽያ ቡናዎች አስፈርመውት ሁለቱ ክለቦች ውዝግብ ውስጥ ገብተው የነበረ ሲሆን ሀዋሳ ከተማዎች ” እኛ ጋር ፈርሞ መልቀቂያ ብቻ ነው የሚቀረው በማለት ክስእና ይግባኝ ብናስገባም ምላሽ አላገኘንም፡፡ እኛ በሱ ምትክ ሌላ ተጫዋቾች ለማምጣት እየምከርን ነው፡፡ ነገር ግን ህግ ስለተጣሰ ያን ለማስከበር እንሞክራለን” ሲሉ የሀዋሳ ከተማ ቴክኒክ ዳይሬክተር አቶ አለምባንተ ማሞ ተናግረዋል፡፡ በኢትዮጵያ እግር ኳስ የተጫዋቾች መመሪያ መሰረት ተጫዋቹ መልቀቂያውን ለሀዋሳ ከተማ አለመስጠቱን ተከትሎ ፌድሬሽኑ ለኢትዮጵያ ቡና ወሰኖ ህጋዊ ቴሴራ በመስጠት የኢትዮጵያ ቡና ንብረት መሆኑን አረጋግጧል፡፡ የመሀል ተከላካዩም ለሁለት አመታት ከቡና ጋር ለመቆየትም ተስማምቷል፡፡

በተያያዘ የክለቡ የቡድን መሪ አቶ ሰይፈ ዘርጋባቸው አሰልጣኝ ድራገን ፖፓዲች ከሀምበሪቾ ካመጧቸው ተጫዋቾች መካከል ድንቅነህ ከበደን ለአዲስ አበባ ከተማ እና በረከትን ለሀምበሪቾ እንዲሁም ሳላምላክ ተገኝን ለባህርዳር ከተማ በውሰት ውል መስጠታቸውን ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም አንድ የቀኝ መስመር ተጫዋች ለማምጣት እየተንቀሳቀሱ እንደሆነም ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *