ብሄራዊ ሊግ

የብሄራዊ ሊግ የምድብ ድልድል ከ20 ቀናት በኋላ እንደሚወጣ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ለመግባት በ24 ክለቦች መካከል የሚደረገውን ፉክክር ድሬዳዋ እንድታስተናግድ መመረጧ የሚታወስ ሲሆን ከየዞናቸው (ብሄራዊ ሊጉ በ8 ዞኖች ተከፋፍሎ እየተካሄደ ይገኛል) ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ ይዘው ያጠናቀቁ በአጠቃላይ 24 ቡድኖች በ6 ምድብ ተከፍለው የማጠቃለያ ውድድራቸውን ያደርጋሉ፡፡

በፌዴሬሽኑ መረጃ መሰረት የምድብ ድልድሉን እጣ የማውጣት ስነ ስርዓት ሐምሌ 23 ቀን 2007 ዓ.ም በድሬዳዋ ስፖርት ኮሚሽን አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ በቀጣዩ ቀን (ሐምሌ 24) ውድድሩ በይፋ ይጀመራል፡፡ እስከ ነሃሴ 17 የሚቆየውን ውድድር በበላይነት የሚያጠናቅቁ ሁለት ክለቦችም ለከርሞ በፕሪሚየር ሊጉ ወልድያ እና ሙገርን ተክተው ይወዳደራሉ፡፡

የሴቶች ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሄራዊ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን በአለም ዋንጫ ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታውን ለማድረግ ዛሬ 3፡00 ላይ ወደ ያውንዴ በሯል፡፡ ወደ ያውንዴ ያመራው ይለኡካን ቡድን ይህንን ይመስላል፡፡

Name Designation Club
ABEBE GELAGAY Team Leader
ASRAT ABATE Coach
SERK ADDIS EWINETU A/Coach
HIWOT ALEMU G.K Coach
MESERET ASSEFA Team Doctor
FIKERTE ZERGA Masseur
WONDIMKUN ALAYU P/R
TIGIST YADETA Player Dedebit
SEBLE TOGA Player Hawassa K
ADDIS NIGUSSIE Player Hawassa K
AMEDA Player Electric
TARIKUA BARGENA Player DireDawa K
WORKINESH MELMELA Player Sidama Bunna
LOZA ABERA Player Dedebit
MEDINA AWOL Player St.Marry Un.
SENAYT BOGALE Player Dedebit
AYNALEM ASAMINEW Player Hawassa K
HASABE MUSO Player DireDawa K
HABTAM ESHETU Player Eth. N. Bank
MARTHA GIRMA Player Dashen Bira
BEZAWIT TESFAYE Player Eth. N. Bank
SERK ADISS GUTA Player Kidus Giorgis
FASIKA BEKELE Player Sidama Bunna
MAEREG TEKO Player Sidama Bunna
HELEN ESHETU Player Dashen Bira
FREWEYIN GEBRU Player Dedebit

 

ጠቅላላ ጉባኤ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ዳኞችና ታዛቢዎች ማህበር ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ሐምሌ 4 ቀን 2007 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በራስ ሆቴል እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡

 

ያጋሩ