የኮንፌድሬሽን ዋንጫ ሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ዛሬ ይጀምራሉ

የ2017 ቶታል ካፍ ኮንፌድሬሽን ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ዛሬ መደረግ ሲጀምሩ ዛሬ ምሽት ፕሪቶሪያ ላይ ሱፐርስፖርት ዩናይትድ የዛምቢያውን ዜስኮ ዩናይትድ ያስተናግዳል፡፡

የደቡብ አፍሪካ ክለቦች በአፍሪካ የክለቦች መድረክ የሚያሳዩት የተዳከመ ውጤትን ተከትሎ ሱፐርስፖርት ዩናይትድ ከምድቡ የማለፍ ተስፋው ጥያቄ ውስጥ ቢገባም የኤሪክ ቲንክለር ስብስብ ብዙዎችን በማስገረም ጭምር ከምድቡ ማለፍ ችሏል፡፡ የአህጉሪቱ የክለቦች ውድድር ላይ ልምድ ያካበተው ዜስኮ ዩናይትድ በዛምቢያ ኤምቲኤን ሊግ ወጥ አቋም ማሳየት ባይችልም በኮንፌድሬሽን ዋንጫው ጥሩ ጉዞ ማድረግ ችሏል፡፡

ሱፐርስፖርት የወሳኝ አጥቂው ጀርሚ ብሮኪ ግልጋሎት ማግኘቱ መልካም የሚባል ዜና ነው፡፡ ብሮኪ በኮንፌድሬሽን ዋንጫ ወሳኝ የሆኑ ግቦችን ለሱፐርስፖርት ማስቆጠር ችሏል፡፡ ከዜስኮ በኩል ኬንያዊው ኢንተርናሽናል ጄሲ ዌሬ ይጠበቃል፡፡

ሁለቱም ክለቦች በየሃገሮቻቸው ሊጎች ባደረጓቸው ጨዋታዎች የተለያየ ውጤትን አስመዝግበዋል፡፡ ሱፐርስፖርት ፕላቲኒየም ስታርስን 2-0 ሲረታ ዜስኮ በቻምየንስ ሊጉ የምድብ ተፋላሚ በነበረው ዛናኮ 3-2 ተረቷል፡፡

የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ቅዳሜ የሚቀጥሉ ሲሆን የሰሜን አፍሪካ ክለቦች እርስበእርስ የሚገናኙባቸው ጨዋታዎች ትኩረት ስበዋል፡፡ የሱዳኑ አል ሂላል ኦባያድ ከቲፒ ማዜምቤ የሚያደርጉት ጨዋታም ይጠበቃል፡፡

የዛሬ ጨዋታ
19፡00 – ሱፐርስፖርት ዩናይትድ ከ ዜስኮ ዩናይትድ (ሉካስ ማስተርፒስስ ሞሪፔ ስታዲየም)

የቅዳሜ ጨዋታዎች

20፡00 – አል ሂላል ኦባያድ ከ ቲፒ ማዜምቤ (ኦባያድ ስታዲየም)
20፡30 – ፋት ዩኒየን ስፖርት ከ ክለብ ስፖርቲፍ ሴፋክሲየን (ኮምፕሌክስ ስፖርቲፍ ሞላይ አል ሃሰን)
20፡45 – ሞሊዲያ ክለብ ደ አልጀር ከ ክለብ አፍሪካ (ስታደ ጁላይ 5 1962)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *