ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ከዚህ ቀደም የ2010 የኢትየጵያ ፕሪምየር ሊግ ጥቅምት 4 እንሚጀምር ቢገልፅም አሁን ግን ሊጉ የሚጀመርበትን ቀን በአንድ ሳምንት በመግፋት ጥቅምት 11 እንደሚጀምር ለክለቦች በላከው ደብዳቤ ገልጿል።
ፌደሬሽኑ ሊጉ የሚጀመርበትን ቀን ለመግፋቱ እንደ ዋነኛ ምክንያት ያስቀመጠው የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌደሬሽን የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫን (ሲቲ ካፕ) ከመስከረም 20 እስከ ጥቅምት 4 ድረስ ለማድረግ መርሃ ግብር በማውጣቱ እና በዝናብ እና በሜዳ ችግር ቀደም ብሎ ውድድሩን ማድረግ አለመቻሉን ከገለፀልን በኃላ ነው ብለዋል።
የኢትየጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ሊጉ የሚጀመርበትን ቀን ብቻ ሳይሆን 25 እና መስከረም 28 እንዲደረግ መርሃ ግብር ተይዞለት የነበረው የ2009 የሊጉ አሸናፊ የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የጥሎ ማለፉ አሸናፊ ወላይታ ድቻ የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ጨዋታንም ወደ ጥቅምት 7 እንዳዞረው ታውቋል። በአዲስ አበባ ስታድየም በደርሶ መልስ መልክ ሊደረጉት የነበሩት ጨዋታዎችም ቀርተው አንድ ጨዋታ ብቻ መስከረም 7 በአዲስ አበባ ስታድየም ይደረጋል፡፡