የቅዱስ ጊዮርጊሱ የግራ መስመር ተከላካይ ዘካርያስ ቱጂ ከክለቡ ጋር የነበረውን ቀሪ የአንድ አመት ውል በስምምነት በማፍረስ ወደ ኢትዮ ኤሌክትሪክ አምርቷል፡፡
ዘካርያስ በ2007 የውድድር አመት ወደ ዋናው ቡድን ካደገ በኋላ በፍጥነት ቋሚ አሰላለፉን ሰብሮ መግባት የቻለ ሲሆን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን መጠራት ችሎ ነበር፡፡ ሆኖም በቀጣዮቹ አመታት በቦታው እምብዛም የመሰለፍ እድል ማግኘት ሳይችል ቀርቶ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ሲሰለፍ ቆይቷል፡፡
እስካሁን 8 አዳዲስ ተጫዋቾችን ባስፈረመው ኢትዮ ኤሌክትሪክ የግራ መስመር ላይ የአለምነህ ግርማን መልቀቅ ተከትሎ በቦታው የተፈጠረውን ክፍተት ይደፍናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡