ወላይታ ድቻ ወሳኝ ተጫዋቾቹን እያጣ ነው

ወላይታ ድቻ በሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ ያደረጉት ተጫዋቾቹን ማጣቱን ቀጥሏል፡፡ የብሄራዊ ቡድኑ አጥቂ ባዬ ገዛኸኝ ወደ መከላከያ ያመራ ሲሆን ለ2 አመት ውስጥ 1.2 ሚልዮን ሊከፈለው ተስማምቷል፡፡

ሌላው የቡድኑ ወሳኝ አማካይ የሆነው ብሩክ ቃልቦሬም ማረፊያውን አዳማ ከነማ አድርጓል፡፡ በመከላከያ እና ባንክ ሲፈለግ የነበረው ብሩክን ለማግኘት አዳማ ከነማ 1.1 ሚልዮን ብር ለ2 አመት ያወጣል ተብሏል፡፡

የቀኝ መስመር ተከላካዩ እሸቱ መናም የብሩክን መንገድ ተከትሎ ወደ አዳማ ከነማ ለመቀላቀል መስማማቱም ተነግሯል፡፡ እሸቱ ከአዳማ ጋር ለ2 አመት በ1 ሚልዮን ብር እንደተስማማም ታውቋል፡፡

ተከላካዩ ተስፋዬ መላኩም ክለቡን የለቀቀ ተጫዋች ነው፡፡ ተስፋዬ ወደ ኤሌክትሪክ ላደረገው ዝውውር ለ2 አመት 1.1 ሚልዮን ብር ሊከፈለው ተስማምቷል፡፡

ያጋሩ