​የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የማጣርያ ዝግጅቱን ነገ ይጀምራል

የኢትዮዽያ ከ17 አመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ለ2018 የዩራጓይ የአለም ዋንጫ ለማለፍ የመጀመርያ የማጣርያ ጨዋታውን በጥቅምት ወር መጀመርያ ያደርጋል፡፡ ለማጣርያው የሚያደርገውን ዝግጅትም ከነገ ጀምሮ ዞላ ኢንተርናሽናል ሆቴል ማረፊያውን በማድረግ ይጀምራል፡፡

ፌዴሬሽኑ የቅዱስ ጊዮርጊሷ አሰልጣኝ ሰላም ዘርአይን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙ የሚታወስ ሲሆን የልደታ ክፍለከተማው ብዙአየሁ ዋዳን ረዳት አሰልጣኝ ፣ የኢትዮጵያ ቡናው (ወንዶች) ውብሸት ደሳለኝን የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ ሆነው ከአሰልጣኟ ጋር የሚሰሩ ይሆናል፡፡

አሰልጣኝ ሰላም ለኬንያው ጨዋታ ዝግጅት 36 ተጫዋቾችን የመረጠች ሲሆን በዝግጅት ወቅትም ስብስቡ ወደ 24 ይቀንሳል ተብሏል፡፡

የቡድን ስብስብ

ግብ ጠባቂዎች

ሳሳሁልሽ ስዩም (አዳማ ከተማ) ፣ እየሩሳሌም ዶራቶ (ንግድ ባንክ) ፣ ናርዶስ ክንፈ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ቤተልሄም (ጌዲኦ ዲላ) ፣ አባይነሽ አርቃሎ (ሀዋሳ ከተማ)

ተከላካዮች

ብዙአየሁ ታደሰ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ፍረወይኒ ገ/ፃድቅ (መከላከያ) ፣ ፅጌ አሳልፈው (ኢትዮጵያ ቡና) ፣ ቤተልሄም አስረሳኸኝ (አዳማ ከተማ) ፣ አበዛሽ ሚጊሶ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ብዙአየሁ አበራ (ደደቢት) ፣ ዘለቃ አሰፋ (ደደቢት) ፣ ታሪኳ ገቢሶ (ንግድ ባንክ) ፣ ፅዮን ማንጁራ – ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ትዕግስት ዳዊት (ሀዋሳ ከተማ)

አማካዮች

ኃይማኖት ግርማ (ጌዲኦ ዲላ) ፣ መዲና ጀማል (ኢ/ወ/ስ/ አካዳሚ) ፣ እየሩሳሌም በነበሩ (ቅድስት ማርያም) ፣ አዳነች ከበደ (ልደታ ክፍለከተማ) ፣ ሶፋኒት ተፈራ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ኪፊያ አብዱራህማን (ጥረት) ፣ ኤልሳቤት ብርሀኑ (መከላከያ) ፣ ዮዲት መኮንን (አዳማ ከተማ) ፣ ሀና አበበ (ኢትዮጵያ ቡና)

አጥቂዎች

አስራት አለሙ (አአ ከነማ) ፣ ሊድያ ጌትነት (ጥረት) ፣ ቤተልሄም ታምሩ (ንግድ ባንክ) ፣ ቤዛዊት ንጉሴ (አቃቂ ቃሊቲ) ፣ ንግስት ኃይሉ (አቃቂ) ፣ ቤተል ጢባ (ጌዲኦ ዲላ) ፣ ቤተልሄም ሰማን (ንግድ ባንክ) ፣ ምስክር ብርሀኑ (ልደታ) ፣  ምንትዋብ ዮሀንስ (ቦሌ ክፍለ ከተማ) ፣ ረድዬት አስረሳህኝ (ቦሌ ክፍለ ከተማ) ፣ ስንታየሁ ማቴዎስ (ሀዋሳ ከተማ) ፣ ነፃነት መና (ሀዋሳ ከተማ)

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *