እንዳለ ከበደ ወደ ቀድሞ ክለቡ ሊመለስ ይችላል

የሲዳማ ቡናው የመስመር አማካይ እንዳለ ከበደ ወደ ቀድሞ ክለቡ አርባምንጭ ከነማ ሊዘዋወር እንደሚችል ተነግሯል፡፡ በ2004 አርባምንጭ ከነማን ለቆ ወደ ሲዳማ ቡና ያቀናው እንዳለ ከበደ በይርጋለሙ ክለብ ዘንድሮ ያሳየው ድንቅ እንቅስቃሴ ለብሄራዊ ቡድን እስከመመረጥም አድርሶታል፡፡
ተጫዋቹ በአርባምንጭ ከነማ በነበረበት ወቅት ከአሰልጣኙ ጋር በነበረው አለመግባባበት ምክንያት ወደ ሲዳማ እንዳመራና አሁን አሰልጣኝ አለማየሁ በሲዳማ ቡና ረዳት አሰልጣኝ ለመሆን መምጣታቸው እንዳለ ክለቡን ለቆ ወደ አርባምንጭ እንዲጓዝ ሊያደርገው ይችላል ተብሏል፡፡
የተጫዋቾቹን ኮንትራት እያራዘመ ያለው ሀዋሳ ከነማም ተጫዋቹን ለማስፈረም ከሚፈልጉት ክለቦች አንዱ ሆኗል፡፡

ያጋሩ