​ሩሲያ 2018፡ ማሊ እና ኮትዲቯር ነጥብ ተጋርተዋል

ወደ 2018ቱ የሩሲያ የዓለም ዋንጫ ለማለፍ የሚደረጉ የአፍሪካ ዞን የማጣሪያ ጨዋታዎች አርብ ምሽት ባማኮ ላይ ሲጀምሩ ማሊ እና ኮትዲቯር ያለግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡ በምድብ ሶስት በተደረገው ጨዋታ ሁለቱም ሃገራት የተለያየ ይሁን እንጂ የማለፍ ከፍተኛ እድል የነበራቸው ሲሆን ውጤቱ ማሊ ከዓለም ዋንጫው ውጪ ያደረገ ሆኗል፡፡
በምድቡ ለሚገኙት ሞሮኮ እና ጋቦን በአንፃሩ ደግሞ መልካም የሚባል ነው፡፡ በጨዋታው ከዝሆኖቹ በተሻለ ንስሮቹ ጫና የጨዋታ የበላይነት የነበራቸው ሲሆን ያለቀላቸው የግብ አድሎችንም በማምከን አምሽተዋል፡፡ በተለይ በመጀመሪያው አጋማሽ ከቅጣት ምት የተሞከረን ኳስ የኮትዲቯር ግብ ጠባቂ ሲልቪያን ጎቦሆ ሲተፋ በቅርቡ የነበረው ሙሳ ዶምቢያ በማይታመን መልኩ ኳስን እና መረብን ሳያገናኝ በግቡ አናት የሰደደው ሙከራ የሚጠቀስ ነው፡፡ ኮትዲቯር ተጋጣሚዋ ላይ ጫና ስትፈጥር ያልታየ ሲሆን በጨዋታው ላይ ሶስት ሙከራዎችን ብቻ ለማድረግ ተገዳለች፡፡ በሁለተኛው አጋማሽ ማሊ በማጣሪያው ልታገኘው የነበረውን የመጀመሪያ ሙሉ ሶስት ነጥብ በግቡ አግዳሚ ምክንያት ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ ውጤቱን ተከትሎ የደረጃ ለውጥ ኮትዲቯር መሪነቷን ማጠናከር አልቻለችም፡፡ ኮትዲቯር በ8 ነጥብ ስትመራ፣ ሞሮኮ በ6 እንዲሁም ጋቦን በ5 ይከተላሉ፡፡ ማሊ በ3 ነጥብ የምድቡ ግርጌ ላይ ትገኛለች፡፡

ዛሬ በርካታ ወሳኝ ጨዋታዎች በተለያዩ የአፍሪካ ከተሞች የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡

የአርብ ውጤት

ማሊ 0-0 ኮትዲቯር

የቅዳሜ ጨዋታ (የሰዓት አቆጣጠሩ በኢትዮጵያ ነው፡፡)

10፡00 – ደቡብ አፍሪካ ከ ቡርኪና ፋሶ (ሶከርሲቲ ስታዲየም (ኤፍኤንቢ))

10፡00 – ዩጋንዳ ከ ጋና (ማንዴላ ናሽናል ስታዲየም)

1፡00 – ናይጄሪያ ከ ዛምቢያ (አክዋ ኢቦም ስታዲየም)

1፡00 – ካሜሮን ከ አልጄሪያ (ስታደ ኦምኒስፖርትስ አማዱ አሂጆ)

2፡00 – ጊኒ ከ ቱኒዚያ (ስታደ 28 ሴፕተምበር)

2፡00 – ሊቢያ ከ ዲ.ሪ. ኮንጎ(ስታደ ሙስጠፋ ቤን ጃኔት)

2፡30 – ኬፕ ቨርድ ከ ሴኔጋል (ፕራያ ስታዲየም)

4፡00 – ሞሮኮ ከ ጋቦን (ኮምፕሌክስ መሃመድ አምስተኛ)

የእሁድ ጨዋታ

2፡00 – ግብፅ ከ ኮንጎ ሪፐብሊክ (ቦርጅ ኤል አረብ ስታዲየም)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *