​የኦሮሚያ ዋንጫ በ4 ከተሞች ይካሄዳል

የ2010 የውድድር አመት የኦሮሚያ ዋንጫ የከፍተኛ ሊግ እና የአንደኛ ሊግ ቡድኖችን በማሳተፍ በአራት የተመረጡ ከተሞች ከጥቅምት 11 ጀምሮ ይከናወናል፡፡
በከፍተኛ ሊግ እና አንደኛ ሊግ የሚሳተፉ የኦሮሚያ ክለቦች ወደ ውድድር ከመግባታቸው አስቀድሞ አቋማቸውን እንዲፈትሹበት በማሰብ ካለፈው አመት ጀምሮ መካሄድ የጀመረውን ይህ ውድድር በኦሮሚያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስር የሚገኘው የኦሮምያ ዳኞችና ኮሚሽነሮች ማህበር በበላይነት የሚያዘጋጀው ይሆናል። አምና በሁለት ከተሞች (ባቱ እና ሰበታ) የተካሄደው ይህ ውድድር ዘንድሮ ወደ አራት ከተሞች ከፍ ያለ ሲሆን በአጠቃላይ 33 ክለቦች ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡

አስተናጋጅ ከተሞች እና ተሳታፊ ክለቦች

ሰበታ ከተማ (11 ቡድኖች)

ሰበታ ከተማ ፣ ጅማ አባ ቡና ፣ ሱሉልታ ከተማ ፣ ለገጣፎ ለገዳዲ ፣ ቡራዮ ከተማ ፣ ነቀምት ከተማ ፣ ሆለታ ከተማ ፣ ቱሉ ቦሎ ፣ ሰንዳፋ በኬ እና ጫንጮ ከተማ ናቸው ።

ባቱ ከተማ (10 ክለቦች)

ባቱ ከተማ ፣ መቂ ከተማ ፣ ገላን ፣ ወንጂ ፣ መተሀራ ስኳር ፣ ቢሸፍቱ ከተማ ፣ ቢሸፍቱ አውቶሞቢል ፣ ጨፌ ዶንሳ ፣ ኢተያ ፣ ኦሮምያ ፖሊስ

ሻሸመኔ (8 ክለቦች)

ሻሸመኔ ከተማ ፣ አርሲ ነገሌ ፣ ሮቤ ከተማ፣ መቱ ከተማ ፣ አሳሳ ከተማ፣ ጎባ ከተማ ፣ አዳባ ፣ ቦኮ ከተማ ፣

ቡሌ ሆራ (4 ክለቦች)

ቡሌ ሆራ ከተማ ፣ ነገሌ ቦረና ፣ አዶላ ከተማ ፤ ቀርጫ ከተማ

የውድድሩ አዘጋጅ ኮሚቴ ለሶከር ኢትዮጵያ እንዳስታወቀው የዕጣ የማውጣት ስነ ስርአት ወደ ፊት የሚገለፅ ሲሆን በየምድቡ አሸናፊ ለሚሆኑ ቡድኖች የዋንጫ ሽልማት የሚሰጥ ይሆናል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *