ሀዋሳ ከነማ ኮንትራት በማደስ ላይ ተጠምዷል

በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ላለመውረድ ሲታገል የነበረው ሀዋሳ ከነማ የወሳኝ ተጫዋቾቹን ኮንትራት አድሷል፡፡ አምበሉ ሙሉጌታን ጨምሮ 5 ተጫዋቾቹን ውል ማደሱም ተነግሯል፡፡

አጥቂው ተመስገን ተክሌ በቡድኑ ከፍተኛው ተከፋይ ያደረገውን ኮንትራት ያደሰ ሲሆን በ2 አመት ውስጥ 1.3 ሚልዮን ብር ሊከፈለው ተስማምቷል፡፡

በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ድንቅ ብቃታቸውን ያሳዩት ጋዲሳ መብራቴ እና ታፈሰ ሰለሞንን ኮንትራት አድሷል፡፡ አንጋፋው የቡድኑ አምበል ሙሉጌታ ምህረት እባ አመለ ኤባ ሌሎች ኮንትራታቸውን በሁለት አመት ያደሱ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

ሀዋሳ ከነማ የኢትዮጵያ ቡናውን የመስመር አማካይ/አጥቂ ኤፍሬም ዘካርያስን በእጁ ያስገባ ሲሆን ብሩክ ቃልቦሬ እና ባዬ ገዛኸኝን ለማስፈረም ያደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል፡፡

ያጋሩ