አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ ተከላካይ አስፈርሟል

የዝውውር መስኮቱን ዘግይቶ የተቀላቀለውና የደቡብ ካስቴል ዋንጫ አሸናፊ የሆነው አርባምንጭ ከተማ ጋናዊው የመሀል ተከላካይ አሌክስ አሙዙን አስፈርሟል።

በክረምቱ በታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ የውጪ ዜግነት ያላቸው ተጫዋቾችን እያስፈረመ የሚገኘው አርባምንጭ ከተማ ለተከላካዩ 18 ቀናት የሙከራ ጊዜ ሰጥቶት የነበረ ሲሆን በቆይታው አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነ ማርያምን በማሳመኑ የአንድ አመት ውል ቀርቦለት ፈርሟል፡፡ የ27 አመቱ አማካይ ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣቱ በፊት ሴኮንዲ ሀስካስ ለተባለ የጋና ክለብ ተጫውቶ አሳልፏል፡፡

አርባምንጭ ከተማ ከላኪ ሰኒ (ናይጄሪያ) እና ሰይዱ ባንሴ (ጋና) በመቀጠል 3ኛ የውጭ ተጫዋች ሲያስፈርም ከዚህ በኋላ ክለቡ ምንም አይነት ተጫዋች እንደማያስፈርም አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም  ለሶከር ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *