ሲዳማ ቡና ራሱን እያጠናከረ ነው

 

በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን የመጀመርያ አጋማሽ አስገራሚ አቋም ያሳየው ሲዳማ ቡና ቡድኑን ከወዲሁ እያጠናከረ ይገኛል፡፡

እንደ ስፖርት ፋና ዘገባ ከሆነ ሲዳማ ቡና የደቡብ ፖሊሱን አማካይ ሚካኤል ለማን አስፈርሟል፡፡ ተጫዋቹ ከሁሉም ክለቦች ቀድሞ ወደ ብሄራዊ ሊጉ ማጠቃለያ ውድድር ማለፉን ባረጋገጠው ደቡብ ፖሊስ ውስጥ ድንቅ አመት አሳልፏል፡፡

ቡድኑ ከአርባምንጭ ከነማ 2 ተጫዋች ማስፈረሙም ታውቋል፡፡ ተከላካዩ አንተነህ ተስፋዬ እና አማካዩ ሙሉአለም መስፍን ወደ ሲዳማ ቡና ለማምራት እያንዳንዳቸው በ2 አመት ውስጥ 1.1 ሚልዮን ብር ሊከፈላቸው ተስማምተዋል ተብሏል፡፡

የቡድኑ አምበል የሆነው ለአለም ብርሃኑም በቡድኑ የሚያቆየውን ኮንትራት በ2 አመት አራዝሟል፡፡ ሲዳ ለለአለም 1.3 ሚልዮን ብር ለመክፈል የተስማማ ሲሆን ይህም ከፍተኛው ተከፋይ ተጫዋች እንዲሆን አድርጎታል፡፡

ያጋሩ