የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ዝውውር – ሀዋሳ ከተማ

በኢትዮጵያ ሴቶች እግር ኳስ ከሚጠቀሱ ጥቂት ጠንካራ ክለቦች አንዱ የሆነው ሀዋሳ ከተማ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በሊጉ 4ኛ ደረጃ ይዞ ሲያጠናቅቅ ደደቢትን በመርታት የጥሎ ማለፍ ቻምፒዮን በመሆን አጠናቋል፡፡ በአመቱ ጉዞው ድንቅ አቋም ያሳዩ 3 ተጫዋቾች ክለቡን መልቀቃቸውን ተከትሎ አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም እና ውላቸውን ያጠናቀቁ ተጫዋቾችነን ውል በማደስ ላይ ይገኛል፡፡

ክለቡ እስካሁን የ5 ተጫዋቾች ተጫዋቾችን ውል ሲያድሱ 13 አዳዲስ ተጫዋች ክለቡን ተቀላቅለዋል፡፡ 4 የተቀነሱ ተጫዋቾችን ጨምሮ 7 ተጫዋቾች ከክለቡ የለቀቁ ሲሆን ከታዳጊ ቡድኑ 6 ተጫዋቾች ወደ ዋናው ቡድን አድገዋል፡፡

የለቀቁ ወሳኝ ተጫዋቾች

ትዕግስት አበራ (ግብ ጠባቂ)፣ ሰብለ ቶጋ (ተከላካይ)፣ አይናለም አሳምነው (አጥቂ)

ውል ያደሱ

ቅድስት ዘለቀ (ተከላካይ)፣ ካሰች ፍሰሀ (ተከላካይ)፣ እታለም አመኑ (አማካይ)፣ ምርቃት ምርቃት ፈለቀ (አጥቂ)፣ ነፃነት መና (አጥቂ)

አዳዲስ ፈራሚዎች

ግብ ጠባቂ

ዳግማዊት መኮንን (ንግድ ባንክ)፣ ገነት ጉታ (ከሆሳዕና ፕሮጀክት)

ተከላካዮች

አይናለም አደሬ (ድሬዳዋ ከተማ)፣ ትዝታ ኃይለ ሚካኤል (ወሊድ መልስ)፣ ብርቱካን ተስፋዬ (ወላይታ ድቻ ፕሮጀክት)

አማካዮች

ሳራ ኬዲዮ (አርባምንጭ ከተማ)፣ ሙሉ ሽፈራው (አርባምንጭ)፣ መሪማ ፈቱ (አዳማ ከተማ)፣ ትዕግስት ዳልጋ (ጥረት ኮርፓሬት)

አጥቂዎች

መሳይ ተመስገን (ከሀዲያ ዞን)፣ አለሚቱ ደራ (አዳማ ከተማ)፣ ልደት ተሎአ (አርባምንጭ ከተማ)፣ እማዋይሽ ይመር (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)

ከታዳጊ ቡድን ያደጉ

ግብ ጠባቂ፡ ነፃነት ነጋሽ

ተከላካይ፡ እመቤት ውብዬ እና ቤተልሄም ውሹ

አማካይ፡ በረከት ጴጥሮስ እና መስከረም ገላና

አጥቂ፡ ፅዮን

ሀዋሳ ከተማ የሴቶች ቡድን በ2002 ከተመሰረተ በኋላ በአካባቢው በተደጋጋሚ የበላይነቱን ያሳየ ሲሆን ባለፉት ሁለት አመታት ለጠንካራዎቹ ደደቢት እነና ንግድ ባንክ ጭምር ፈታኝ የሆነ ተፎካካሪ ቡድን ገንብቷል፡፡ ከሌሎች ክለቦች በተለየም የሴቶች ታዳጊ ቡድን በማቋቋም በርካታ ተስፈኛ ተጫዋቾችን ለኢትዮጵያ እግርኳስ በማበርከት ላይ ይገኛል፡፡

የቡድኑ አሰልጣኝ ዮሴፍ ገ/ወልድ ስለ ዝግጅታቸው ለሶከር ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ በሰጡት አስተያየት ወሳኝ ተጫዋቾች ቢለቁባቸውም ተፎካካሪ ለመሆን እየተዘጋጁ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ “በየአመቱ በርካታ ተጫዋቾች ከክለቡ ይለቃሉ፡፡ ከዚህ ቀደም ከታች ያመጣናቸው ሎዛ አበራ፣ አስራት አለሙ እና ነህሚያ አበራ ዘንድሮ ደግሞ ከሎዛ በመቀጠል በኮከብ ግብ አግቢነት ያጠናቀቀችሁ አይናለም አሳምነው፣ ሰብለ ቶጋ እና ግብ ጠባቂያችን ትዕግስት አበራ ክለቡን ለቀዋል፡፡ በየአመቱ አዳዲስ ተጫዋቾችን ብናሳድግም የክለቡ የፋይናንስ ሁኔታ እና የአመራሩ ትኩረት ማጣት ተጫዋቾች እንዲለቁብን እና በተደደጋሚ ውጤት እንዳናመጣ መሰናክል ሆኖብናል፡፡ ሆኖም ከዚህ ቀደም እንደማደርገው ታዳጊዎች እና ልምድ በሌላቸው የተጫዋቾች ስብስብ የፎርማት ለውጥ በተደረገበት ውድድር ላይ ተፎካካሪ ለመሆን ዝግጅት ጀምረናል፡፡” ብለዋል፡፡

ሀዋሳ ከተማ ዝግጅቱን ካለፈው እሁድ ጀምሮ በዛው ሀዋሳ በቀን ሁለት ጊዜ ማድረግ የጀመረ ሲሆን በመጀመርያ ሳምንት የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ከሜዳው ውጪ ድሬዳዋ ከተማን የሚገጥም ይሆናል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *