ካፍ የአሰልጣኞች ስልጠና ፍቃድ መስጠቱን በጊዜያዊነት አቆመ

የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌድሬሽን (ካፍ) የአሰልጣኞች ስልጠና በኤ፣ ቢ እና ሲ ደረጃ ፍቃድ መስጠት ለግዜው ማቆሙን አስታውቋል፡፡ ካፍ የአሰልጣኞች ስልጠና የሚሰጥበትን መንገድ ለማሻሻል በማሰብ ነው ስልጠናውን ያቆመው፡፡

ካፍ ለረጅም ግዜያት ሲተችበት የነበረውን የአሰልጣጠን መንገድ እንዲያሻሽል በተደጋጋሚ ከእግርኳስ ባለሙያዎች ጥሪ ሲቀርብለት ቢስተዋልም እርምጃ ከመውሰድ ሲቆጠብ ይስተዋላል፡፡ አሁን ላይ ፕሬዝደንት አህመድ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ ግን የደረጃ አሰጣጡን ለማሻሻል ጥረቶችን ጀምሯል፡፡ ለዚህም ሲባል የደረጃ አሰጣጥ ትምህርቱን ለግዜውም ቢሆንም ማቋረጡን  እና  ማሻሻያዎች ከተደረጉ በኃላ ትምርቶቹ መሰጠት እንደሚጀምሩ ታውቋል፡፡

የትምርቱን ጥራት ምክንያት በማድረግ አንዳንድ የአፍሪካ ክለቦች ከሀገራቸው አሰልጣኞች ይልቅ ፊታቸውን ከአውሮፓ እና ደቡብ አሜሪካ ወደሚመጡ አሰልጣኞች አዙረዋል፡፡ ከስልጠናው ባሻገር አሰልጣኞች እራሳቸውን ለማሻሻል የግል ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው የሚጠቁሙ ባለሙያዎችም አሉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *