​ሳላዲን ሰዒድ በካፍ ኮከብ ሽልማት 30 እጩዎች ውስጥ ተካቷል

የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌድሬሽን (ካፍ) በጥር 2018 በጋና መዲና አክራ ለሚያካሂደው የአቲዮ ካፍ የአመቱ ምርጥ ተጫዋች ሽልማት እጩዎችን ዛሬ ከሰዓት ይፋ አድርጓል፡፡ የአመቱ ምርጥ የአፍሪካ ተጫዋች እና የአመቱ ምርጥ በአፍሪካ የሚጫወት ተጫዋች ሽልማት በሚል በሁለት በተከፈለው ሽልማት ላይ ኢትዮጵያዊው አጥቂ ሳላዲን ሰዒድ መካተት ችሏል፡፡

ሳላዲን በአፍሪካ የሚጫወት ምርጥ ተጫዋቾ ሽልማት 30 እጩዎች ውስጥ የገባ ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ሲሆን ከ2013 አንስቶ ይህ ለመጀመሪያ ግዜ ነው፡፡ ሳላዲን በቶታል ካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ሰባት ግቦች በውድድር ዘመኑ በማስቆጠር የኮከብ ግብ አግቢነቱን ከኤስፔራንስ እና የቱኒዚያው ኮከብ ጠሃ ያሲን ኬኔሲ ጋር በጣምራ እየመራ ይገኛል፡፡ ለክለቡ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ2017ቱ ቻምፒየንስ ሊግ ለመጀመሪያ ግዜ እስከምድብ እንዲጓዝም ቁልፍ ሚናን ከተጫወቱ ተጫዋቾች መካከል ሳላዲን ይጠቀሳል፡፡ በ2013 አዳነ ግርማ እና ጌታነህ ከበደ በተመሳሳይ ሽልማት 25 ተጫዋቾች ዝርዝር ውስጥ መግባታቸው ይታወሳል፡፡ በውድድሩ ላይ በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ እና ኮንፌድሬሽን ዋንጫ ላይ እስከግማሽ ፍፃሜ ከተጓዙ ቡድኖች ውስጥ አብዛኞቹ ተጫዋቾቹ መካተት ችለዋል፡፡

በዓመቱ ምርጥ የአፍሪካ ተጫዋች እጩዎች ውስጥ 4 ተጫዋቾች (ዴኒስ ኦኒያንጎ፣  ፐርሲ ታኦ፣ አሊ ማሎል እና ፋክሰን ካፑምቡ) ብቻ በአህጉሪቱ የሚጫወቱ ሲሆኑ በአውሮፓ የሚጫወቱ አፍሪካዊያን ከዋክብት ዝርዝሩን ተቆጣጥረውታል፡፡ በአፍሪካ የሚጫወት ምርጥ ተጫዋች ዝርዝር ውስጥ የዩጋንዳው ግብ ጠባቂ እና የዓምና የሽልማቱ አሸናፊ ዴኒስ ኦኒያንጎ፣ አህመድ ፋቲ እና አሪስቲድ ባንሴ የመሳሰሉ ተጫዋቾች መካተት ችለዋል፡፡ በዋናው ሽልማት ዘርፍ እንደመሃመድ ሳላህ፣ ኤሪክ ቤዬ፣ ቪክቶር ሞሰስ፣ ሳድዬ ማኔ እና የአፍሪካ ዋንጫ ኮከብ የተባለው ክሪስቲያን ባሶጎግ ተካተዋል፡፡

ሽልማቱ በጥር 4 2018 የሚሰጥ ሲሆን ከሽልማት ስነ-ስርዓቱ አስቀድሞ በሁለቱም ምድቦች የተካተቱ 30 ተጫዋቾችን ወደ 10 የመቀነስ ስራ ይሰራል፡፡ በመቀጠልም እጩዎቹ ወደ 3 ዝቅ የሚደረጉ ይሆናል፡፡ የብሄራዊ ቡድኖች አሰልታኞች ወይም የቴክኒክ ዳይሬክተሮች፣ የካፍ ቴክኒክ እና ልማት ኮሚቴ አባላት እና የሚዲያ ኤክስፐርቶች ፓናል በሚሰጡት ድምፅ አሸናፊውን የሚለይ ይሆናል፡፡ አምና በተመሳሳይ ውድድር ሪያድ ማህሬዝ የዓመቱ ምርጥ የአፍሪካ ተጫዋች ተብሎ ሲመረጥ ዴኒስ ኦኒያንጎ በአፍሪካ የሚጫወት ምርጥ ተጫዋች ተብሎ መመረጣቸው አይዘነጋም፡፡

የአፍሪካ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች እጩዎች ዝርዝር
አሊ ማሎል (ቱኒዚያ – አል አህሊ)

በርትራንድ ትራኦሬ (ቡርኪና ፋሶ – ሊዮን)

ሴድሪክ ባካምቡ (ዲ.ሪ. ኮንጎ – ቪያሪያል) 

ክሪስቲያን አትሱ (ጋና – ኒውካስል ዩናይትድ)

ክሪስቲያን ባሶጎግ (ካሜሮን – ሄናን ዢያኒ) 

ዴኒስ ኦኒያንጎ (ዩጋንዳ – ማሜሎዲ ሰንዳውንስ)

ኤሪክ ቤዬ (ኮትዲቯር – ማንቸስተር ዩናይትድ)

ኤሳም ኤል-ሀዳሪ (ግብፅ – አል ታዎን)

ፋብሪስ ኦንዳ (ካሜሮን – ሲቪያ)

ፋክሰን ካፑምቡ (ዛምቢያ – ዜስኮ ዩናይትድ)

ጃን ሚሼል ሴሪ (ኮትዲቯር – ኒስ)

ጁኒየር ካባናንጋ (ዲ.ሪ. ኮንጎ – አስታና)

ካሪም ኤል አህመዲ (ሞሮኮ – ፋይኖርድ)

ኬይታ ባልዴ (ሴኔጋል – ሞናኮ)

ካሊድ ቦታይብ (ሞሮኮ – የኒ ማልታያስፖር)

ምባዋና ሳማታ (ታንዛኒያ -ጌንክ)

ሚካኤል ኦሉንጋ (ኬንያ – ጂሮና)

መሃመድ ሳላህ (ግብፅ – ሊቨርፑል)

ሞሰስ ማሬጋ (ማሊ – ፖርቶ)

ናቢ ኬይታ (ጊኒ – አርቢ ላይፕዢሽ)

ፐርሲ ታኦ (ደቡብ አፍሪካ – ማሜሎዲ ሰንዳውንስ)

ፒየር ኤምሪክ ኦባምያንግ (ጋቦን – ቦሩሲያ ዶርቱመንድ)

ሳድዮ ማኔ (ሴኔጋል፣ ሊቨርፑል)

ቶማስ ፓርቴ (ጋና – አትሌቲኮ ማድሪድ)

ቪክቶር ሞሰስ (ናይጄሪያ – ቼልሲ)

ቪንሰንት አቡበከር (ካሜሮን – ፖርቶ)

ዊሊያም ትሮስት-ኢኮንግ (ናይጄሪያ – ቦራስፖር)

ያሲን ብራሂሚ (አልጄሪያ – ፖርቶ)

የሱፍ ሳክኒ (ቱኒዚያ – አል ዱሃል)

የቭስ ቢሶማ (ማሊ – ሊል)

አሊ ማሎል

በአፍሪካ የሚጫወቱ የአመቱ ምርጥ ተጫዋች እጩዎች ዝርዝር
አሽራፍ ቤንሻሪኪ (ሞሮኮ – ዋይዳድ ካዛብላንካ)

አህመድ ፋቲ (ግብፅ – አል አህሊ)

አልካላይ ባንጉራ (ጊኒ – ኤትዋል ደ ሳህል)

አሊ ማሎል (ቱኒዚያ – አል አህሊ)

አሪስቲድ ባንሴ (ቡርኪና ፋሶ – አል መስሪ)

አይመን ማጂድ (ሞሮኮ – ፉስ ራባት)

አይመን ማትሎቲ (ቱኒዚያ – ኤትዋል ደ ሳህል)

ቤን ማላንጎ (ዲ.ሪ. ኮንጎ – ቲፒ ማዜምቤ)

ዲን ፈርማን (ደቡብ አፍሪካ – ሱፐርስፖርት ዩናይትድ)

ዴኒስ ኦኒያንጎ (ዩጋንዳ – ማሜሎዲ ሰንዳውንስ)

ኤልሳማኒ ሳደልዲን (ሱዳን – ኤል ሜሪክ)

ፋክሰን ካፑምቡ (ዛምቢያ – ዜስኮ ዩናይትድ)

ፋውዚ ካውቺ (አልጄሪያ – ኤምሲ አልጀር)

ጂኦፍሪ ሴሬንኩማ (ዩጋንዳ – ኬሲሲኤ)

ጀርሚ ብሮኪ (ኒው ዚላንድ – ሱፐርስፖርት ዩናይትድ)

ጁኒየር አጃዬ (ናይጄሪያ – አል አህሊ)

ካሪም አዎዲ (ቱኒዚያ – ሴፋክሲየን)

መሃመድ ሚፍታህ (አልጄሪያ – ዩኤስኤም አልጀር)

መሃመድ ኦንዠም (ሞሮኮ – ዋይዳድ ካዛብላንካ)

ሙኤድ ኤላፊ (ሊቢያ – አል አሃሊ ትሪፖሊ)

ነስረዲን አህመድ (ሱዳን – ሂላል ኦብዬድ)

ኦሳማ ዳርፋሎ (አልጄሪያ – ዩኤስኤም አልጀር)

ፐርሲ ታኦ (ደቡብ አፍሪካ – ማሜሎዲ ሰንዳውንስ)

ሳቤሎ ንድዚንሳ (ስዋዚላንድ – ምባባኔ ስዋሎስ)

ሳብር ካሊፋ (ቱኒዚያ – ክለብ አፍሪካ)

ሳላዲን ሰዒድ (ኢትዮጵያ – ቅዱስ ጊዮርጊስ)

ሲልቪያን ጎቦሆ (ኮትዲቯር – ቲፒ ማዜምቤ)

ቴዲ ኢቲኪያማ (ዲ.ሪ. ኮንጎ – ኤኤስ ቪታ ክለብ)

ጠሃ ያሲን ኬኒሲ (ቱኒዚያ – ኤስፔራነስ ደ ቱኒዝ)

ታሬቅ ሃማድ (ግብፅ – ዛማሌክ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *