አብዱልከሪም መሀመድ ወደ ኢትዮጵያ ቡና?

የሲዳማ ቡናው የመስመር ተከላካይ አብዱልከሪም መሃመድ ሲዳማ ቡናን ለቆ ወደ ኢትዮጵያ ቡና ለመቀላቀል ከጫፍ መድረሱን ከምንጮቻችን የደረሱን መረጃዎች አመልክተዋል፡፡

ወጣቱ የመስመር ተከላካይ ኢትዮጵያ ቡናን ለመቀላቀል ፍላጎቱን ያሳየ ሲሆን በሚከፈለው ዙርያ ለመስማማት እየተነጋገሩ መሆኑ ታውቋል፡፡ ተጫዋቹ እና ክለቡ ከስምምነት ላይ ከደረሱም በመጪዎቹ ቀናት ሊፈርም እንደሚችል ተነግሯል፡፡ ክለቡ ከተጫዋቹ የተጠየቀው ገንዘብ እስከ 1.5 ሚልዮን እንደሆነና ክለቡ ገንዘቡን ለማስቀነስ ጥረት ላይ መሆኑም ተነግሯል፡፡

በ2005 ክረምት ሃዋሳ ከነማን ለቆ ሲዳማ ቡናን የተቀላቀለው አብዱልከሪም በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ድንቅ ብቃታቸውን ካሳዩ ተጫዋቾች አንዱ ሲሆን ለብሄራዊ ቡድን ጨዋታም አድርጓል፡፡ በውድድር ዘመኑ መጨረሻ ጉዳት የገጠመው አብዱልከሪም ከጉዳቱ አገግሞ በሃዋሳ በግሉ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እየሰራ ይገኛል፡፡

በተያያዘ ዜና ሲዳማ ቡና በመውጫ በር ላይ የሚገኘው እንዳለ ከበደን በክለቡ ለማቆየት እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑ ታውቋል፡፡ ተጫዋቹ ከአርባምንጭ ከነማ እና ሀዋሳ ከነማ ጋር ስሙ እየተያያዘ ይገኛል፡፡

ያጋሩ