ኤሌክትሪክ 8 ተጫዋቾቹን ዛሬ በይፋ አስፈርሟል

ኤሌክትሪክ ዛሬ ውል ለማደስ የተስማማቸውን እና አዳዲስ ተጫዋቾቹን ፌዴሬሽን ወስዶ አስፈርሟቸዋል፡፡ ክለቡ ያስፈረማቸው ተጫዋቾች ከዚህ በፊት በክለቡ ለመቀጠል የተስማሙት እና አዲስ ለመቀላቀል ከስምምነት የደረሱትን ነው፡፡ አዲስ ነጋሽ ፣ አወት ገ/ሚካኤል ፣ አሳልፈው መኮንን እና በረከት ተሰማ ከክለቡ ጋር ያላቸውን ውል ማደሳቸውን ዛሬ በፊርማቸው ሲያረጋግጡ ብሩክ አየለ ፣ ሃብታሙ መንገሻ እና አለምነህ ግርማ ለክለቡ በፌዴሬሽን ተገኝተው በይፋ የፈረሙ አዳዲስ ተጫዋቾች ናቸው፡፡ ክለቡ ላስፈረማቸው ተጫዋቾች ለእያንዳንዳቸው ከ850ሺህ እስከ 1.3 ሚልዮን ብር በ2 አመታት ውስጥ ይከፍላል ተብሏል፡፡

ክለቡ በቃል ደረጃ የተስማማቸው የወላይታ ድቻዎቹ አሸናፊ ሽብሩ እና ተስፋዬ መላኩ ለእረፍት ክፍለ ሃገር የሚገኙ በመሆናቸው ከእረፍት ሲመለሱ ለክለቡ በይፋ ይፈርማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ያጋሩ