በጥር ወር በሚስተናገደው የአፍሪካ ሃገራት ቻምፒዮንሺፕ (ቻን) የምድብ ድልድሉ አርብ ምሽት በሞሮኮ መዲና ራባት ይፋ ሆኗል፡፡ በሆቴል ሶፊቴል በተደረገው የዕጣ ማውጣት ስነ-ስርዓት የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪከ ዞን በሶስት ሃገራት ተወክሏል፡፡
ለአምስተኛ ግዜ በሚካሄደው የቻን ውድድር አዘጋጇ ሞሮኮ በምድብ አንድ ከጊኒ፣ ሱዳን እና ሞሪታንያ ጋር ስትደለደል ዩጋንዳ በምድብ ሁለት ተገኝታለች፡፡
ኢትዮጵያን አሸንፋ ሁለተኛ እድሏን በአግባቡ የተጠቀመችው ሩዋንዳ በበኩሏ በምድብ ሶስት ከሊቢያ እና ናይጄረያ ጋር ተፋጣለች፡፡ ውድድሩን በአራት ከተሞች የሚካሄድ ይሆናል፡፡ ካዛብላንካ፣ ማራካሽ፣ ታንገ እና አጋድር ውድድሮቹን እንዲያስተናግዱ የተመረጡ የሞሮኮ ከተሞች ናቸው፡፡ በመክፈቻው ጨዋታ ሞሮኮ ሞሪታንያን በካዛብላንካው ስታደ መሃመድ አምስተኛ ታስተናግዳለች፡፡
የምድብ ድልድሉ ይህንን ይመስላል
ምድብ 1 (ካዛብላንካ)
ሞሮኮ፣ ጊኒ፣ ሱዳን፣ ሞሪታንያ
ምድብ 2 (ማራካሽ)
ኮትዲቯር፣ ዛምቢያ፣ ዩጋንዳ፣ ናሚቢያ
ምድብ 3 (ታንገ)
ሊቢያ፣ ናይጄሪያ፣ ሩዋንዳ፣ ኤኳቶሪያል ጊኒ
ምድብ 4 (አጋድር)
አንጎላ፣ ካሜሮን፣ ኮንጎ ሪፐብሊክ፣ ቡርኪና ፋሶ
የቻን ውድድር ሙሉ ፕሮግራም (በኢትዮጵያ ቀን እና ሰዓት አቆጣጠር)
ጥር 5/2010
4፡30 – ሞሮኮ ከ ሞሪታንያ (ካዛብላንካ)
ጥር 6/2010
11፡30 – ጊኒ ከ ሱዳን (ካዛብላንካ)
1፡30 – ኮትዲቯር ከ ናሚቢያ (ማራካሽ)
4፡30 – ዛምቢያ ከ ዩጋንዳ (ማራካሽ)
ጥር 7/2010
1፡30 – ሊቢያ ከ ኤኳቶሪያል ጊኒ (ታንገ)
4፡30 – ናይጄሪያ ከ ሩዋንዳ (ታንገ)
ጥር 8/2010
1፡30 – አንጎላ ከ ቡርኪና ፋሶ (አጋድር)
4፡30 – ካሜሮን ከ ኮንጎ ሪፐብሊክ (አጋድር)
ጥር 9/2010
1፡30 – ሞሮኮ ከ ጊኒ (ካዛብላንካ)
4፡30 – ሱዳን ከ ሞሪታንያ (ካዛብላንካ)
ጥር 10/2010
1፡30 – ኮትዲቯር ከ ዛምቢያ (ማራካሽ)
4፡30 – ዩጋንዳ ከ ናሚቢያ (ማራካሽ)
ጥር 11/2010
1፡30 – ሊቢያ ከ ናይጄሪያ (ታንገ)
4፡30 – ሩዋንዳ ከ ኤኳቶሪያል ጊኒ (ታንገ)
ጥር 12/2010
1፡30 – አንጎላ ከ ካሜሮን (አጋድር)
4፡30 – ኮንጎ ሪፐብሊክ ከ ቡሪኪና ፋሶ (አጋድር)
ጥር 13/2010
4፡00 – ሱዳን ከ ሞሮኮ (ካዛብላንካ)
4፡00 – ሞሪታንያ ከ ጊኒ (ማራካሽ)
ጥር 14/2010
4፡00 – ዩጋንዳ ከ ኮትዲቯር (ማራካሽ)
4፡00 – ናሚቢያ ከ ዛምቢያ (ካዛብላንካ)
ጥር 15/2010
4፡00 – ሩዋንዳ ከ ሊቢያ (ታንገ)
4፡00 – ኤኳቶሪያል ጊኒ ከ ናይጄሪያ (አጋድር)
ጥር 16/2010
4፡00 – ኮንጎ ሪፐብሊክ ከ አንጎላ (አጋድር)
4፡00 – ቡርኪና ፋሶ ከ ካሜሮን (ታንገ)
የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች በአራቱም ከተሞች በጥር 19 እና 20/2010
የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች በካዛብላንካ እና ማራካሽ በጥር 23/2010
የደረጃ ጨዋታ በጥር 26/2010 ማራካሽ ላይ፡፡
የፍፃሜ ጨዋታ በጥር 27/2010 ካዛብላንካ ላይ፡፡