ባሪቶ በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫቸው…

አዲሱ የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ማርያኖ ባሬቶ ዛሬ ረፋድ ለመጀመርያ ጊዜ በኢንተር-ኮንትኔንታል ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በርካታ ሃሳቦችን አንስተዋል፡፡ አሰልጣኙ በብሄራዊ ቡድኑ እና አጠቃላይ የኢትዮጵያ እግርኳስ ዙርያ ከሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ውስጥ የሚከተሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

-ብሄራዊ ቡድናችን በቅርቡ ከቱርክ ጋር ሊጫወት ይችላል

‹‹ በእርግጠኝነት እንደምንጫወት ማረጋገጫ ልሰጥ ባልችልም በኦገስት መጨረሻ ጨዋታ እናደርጋለን፡፡ ለዚህም ዝግጅት እያደረግን ነው››

-ከ20 አመት በታች ሊግ ያስፈልጋል

‹‹ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽን ልክ እስከ ከ17 አመት በታች ውድድር ሁሉ ከ20 አመት በታች ሊግ ሊያዘጋጅ ይገባል፡፡ ለብሄራዊ ቡድኑ እና ለክለቦቹ ወጣቶችን የሚመግብ ሊግ ኢትዮጵያ ያስፈልጋታል፡፡ ››

-የሊጉ ጨዋታዎች በቂ አይደሉም

‹‹ በአመት ውስጥ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሚደረጉት ጨዋታዎች በቂ አይደሉም፡፡ የክለቦች ቁጥር ቢጨመር ፣ በውድድር ዘመኑ ክለቦች እርስ በእርስ የሚያደርጉት ጨዋታ ከ2 ወደ 3 ቢያድግ አልያም ተጨማሪ ውድድሮች ቢዘጋጁ መልካም ነው፡፡ ››

-ስለ ምክትሎቹ

ከፋሲል ተካልኝ እና ዳንኤል ፀሃዬ ጋር እሰራሁ ነው፡፡ የተጫዋቾቹን ምርጫ ያከናወንኩትም ከእነሱ ጋር ተማክሬ ነው፡፡ ››

– ስለ አልጄርያ

‹‹ አልጄርያን በአለም ዋንጫው ተመልክተናታል፡፡ ጠንካሮች ቢሆንም እነርሱን ለማሸነፍ ጠንክረን እየሰራን ነው፡፡

– አካል ብቃት

‹‹ የኢትዮጵያ ተጫዋቾች የአካል ብቃት ችግር ያለባቸው አይመስለኝም፡፡ ኢትዮጵያ የአትሌቶችች ሃገር በመሆኗ በዚህ በኩል ችግር ይኖራል ብዬ አላምንም፡፡ ››

ያጋሩ