ከህዳር 24 ጀምሮ በኬንያ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ እግርኳስ ካውንስል (ሴካፋ) ዋንጫ የሚካፈለው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለሚያደርገው ዝግጅት አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ 27 ተጫዋቾችን ጠርተዋል፡፡
አሰልጣኙ በስብስባቸው ዝርዝር ውስጥ 9 ተጫዋቾች ለመጀመርያ ጊዜ የተመረጡ ሲሆን ለብሄራዊ ቡድን በርካታ ጨዋታ ያደረጉ ተጫዋቾችም በዝርዝሩ ውስጥ ተካተዋል፡፡
ለብሔራዊ ቡድኑ የተጠሩት ተጫዋቾች እስከ ነገ ሆቴል እንሚሰባሰቡ የተገለፀ ሲሆን ከነገ በስቲያ በይፋ ልምምዳቸውን እንደሚጀምሩ ታውቋል፡፡
ዝርዝር
ግብ ጠባቂዎች (3)
ታሪክ ጌትነት (ደደቢት) ፣ በረከት አማረ (ወልዋሎ) ፣ ተክለማርያም ሻንቆ (ሀዋሳ ከተማ)
ተከላካዮች (8)
ቴዎድሮስ በቀለ (መከላከያ) ፣ አበበ ጥላሁን (ሲዳማ ቡና) ፣ አበባው ቡታቆ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ አናጋው ባደግ (ድሬዳዋ ከተማ) ፣ ግርማ በቀለ (ኤሌክትሪክ) ፣ አምሳሉ ጥላሁን (ፋሲል) ፣ ተመስገን ካስትሮ (አርባምንጭ ከተማ) ፣ ኄኖክ አዱኛ (ጅማ አባ ጅፋር)
አማካዮች (9)
ሳምሶን ጥላሁን (ኢትዮጵያ ቡና) ፣ ተስፋዬ አለባቸው (ወልዲያ) ፣ ከነአን ማርክነህ (አዳማ) ፣ እንዳለ ከበደ (አርባምንጭ) ፣ በኃይሉ ተሻገር (ኤሌክትሪክ) ፣ ብሩክ ቃልቦሬ (ወልዲያ) ፣ መስዑድ መሐመድ (ኢትዮጵያ ቡና) ፣ ዮናስ ገረመው (ጅማ አባ ጅፋር) ፣ ፍሬው ሰለሞን (ሀዋሳ ከተማ)
አጥቂዎች (7)
አቡበከር ሳኒ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ አብዱራህማን ሙባረክ (ፋሲል ከተማ) ፣ አዲስ ግደይ (ሲዳማ ቡና) ፣ ዳዋ ሆቴሳ (አዳማ ከተማ) ፣ አማኑኤል ገብረሚካኤል (መቐለ ከተማ) ፣ አቤል ያለው (ደደቢት) ፣ ፀጋዬ ብርሀኑ (ወላይታ ድቻ)