ካሜሩን በ2019 ለምታስተናግደው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የሚደረጉ የምድብ የማጣሪያ ጨዋታዎች የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌድሬሽን (ካፍ) ለውጥ ማድረጉን ባሳለፍነው ሳምንት ማስታወቁ ይታወቃል፡፡ በመጋቢት 2018 የሚደረጉት ጨዋታዎችንም ወደ መስከረም 2018 ማሻገሩ ይታወሳል፡፡
ካፍ ለውጥ ያደረገበት ምክንያት አህጉሪቱን ወክለው በዓለም ዋንጫው የሚካፈሉ ሃገራት በቂ የዝግጅት እና የአቋም መለኪያ ጨዋታዎች እንዲደረጉ ታስቦ ነው፡፡ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታዎች ከመጋቢት 10 – 18/2010 ከመደረግ ይልቅ በቀን ለውጡ ምክንያት በፊፋ ካላንደር መሰረት ሃገራት የወዳጅነት ጨዋታን ማድረግ ይችላሉ፡፡
ካፍ ከወዲሁ የማጣሪያ ጨዋታዎች ሊደረጉባቸው የሚችሉበት ወር እና ቀናት ይፋ አድርጓል፡፡ በዚህም መሰረት የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ በኢትዮጵያ የቀን አቆጣጠር መሰረት በነሃሴ 2010 እና መስከረም 2011 መካከል ባሉት ቀናት ሲካሄድ ሶስተኛ እና አራተኛ ጨዋታዎች በአንድ ሳምንት ልዩነት በመስከረም 2011 ይካሄዳሉ፡፡ በህዳር እና መጋቢት 2011 ደግሞ የመጨረሻዎቹ ሁለት ጨዋታዎች የሚካሄዱ ይሆናሉ፡፡
የቀን ለውጡ (በኢትዮጵያ አቆጣጠር) እና የምድብ 6 ጨዋታዎች
የምደብ ሁለተኛ ጨዋታ ከነሃሴ 28/2010 – መስከረም 1/2011 ባሉት ቀናት
ኢትዮጵያ ከ ሴራ ሊዮን
ኬንያ ከ ጋና
ምድብ ሶስተኛ እና አራተኛ ጨዋታ ከመስከረም 28 – ጥቅምት 6/2011 ባሉት ቀናት
ጋና ከ ሴራ ሊዮን
ኢትዮጵያ ከ ኬንያ
ሴራ ሊዮን ከ ጋና
ኬንያ ከ ኢትዮጵያ
የምድብ አምስተኛ ጨዋታዎች ከህዳር 3 – 11/2011 ባሉት ቀናት
ኢትዮጵያ ከ ጋና
ኬንያ ከ ሴራ ሊዮን
የምደብ ስድስተኛ ጨዋታዎች ከመጋቢት 9 – 17/2011 ባሉት ቀናት
ሴራ ሊዮን ከ ኢትዮጵያ
ጋና ከ ኬንያ