ሳላዲን በአልጀሪያ ከፍተኛ ደሞዝ ይከፈለዋል

ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል አጥቂ ሳላዲን ሰዒድ ባሳለፍነው ሳምንት የግብፁን አል አሃሊን ለቆ የአልጄሪያውን ኤምሲ አልጀርን ተቀላቅሏል፡፡ ሳላ ለአልጀሪያው ክለብ የሁለት ዓመት ውል መፈረሙ ይታወሳል፡፡ አሁን ባገኘነው መረጃ መሰረት ሳላ በኤምሲ አልጀር 27,500 ዩሮ ወርሃዊ ደሞዝ እንደሚከፈለው ማረጋገጥ ችለናል፡፡ ሳላዲን ከኤምሲ አልጀር የተለያዩ ጥቅማጥቅሞች እንደሚቀርቡለትም ተነግሯል፡፡

ኤምሲ አልጀር ለሳላዲን 3 ሚሊየን የአልጀሪያ ዲናር ወይንም ወደ 27,500 ዩሮ ወርሃዊ ደሞዝ ለመክፈል መስማማቱ ታውቋል፡፡ የአልጀሪ መዲና ክለብ የሆነው ኤምሲ አልጀር በቀጣይ ውድድር ዘመን ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ ለመቅረብ ተጫዋቾችን አስፈርሟል፡፡

11700831_933093326751354_3595255459340632745_n

በ2014/15 ውድድር ዘመን ከመውረድ በአንድ ነጥብ ብቻ የተረፈው ኤምሲ አልጀር ያስፈረማቸው ተጫዋቾችም የደሞዝ አከፋፈል ስርዓቱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚያሳድሩ ከአልጀሪያ የሚወጡ መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡ ኤምሲ አልጀርን በባለቤትነት የሚያስተዳድረው የአልጀሪያው ሶናትራች በክለቡ የደሞዝ መናር ደስተኛ አይደለም፡፡ ሶናትራች በአልጀሪያ መንግስት ስር ያለ የነዳጅ፣ የተፈጥሮ ጋዝ እና የፔትሮሊየም ኬሚካል አምራች ኮርፓሬሽን ነው፡፡ ኤምሲ አልጀር ለተጫዋቾች ደሞዝ በወር ከ30 ሚሊየን የአልጄሪያ ዲናር በላይ ይከፍላል፡፡

ያጋሩ