በ8 ክለቦች መካከል በሀዋሳ ሲካሄድ የሰነበተው የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የጥሎ-ማለፍ ዙር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡
በግማሽ ፍፃሜው ሀዋሳ ከነማን አሸንፎ ወደ ፍፃሜው የተሸጋገረው ንግድ ባንክ በፍፃሜው ደደቢትን አሸንፎ የአምና ክብሩን አስጠብቋል፡፡ የጨዋታው መደበኛ መርሃ ግብር ካለግብ በአቻ ውጤት የተጠናቀቀ ሲሆን አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠው የፍፁም ቅጣት ምት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 5 – 4 በሆነ ውጤት አሸንፎ ቻምፒዮን ሆኗል፡፡
ከውድድሩ መጠናቀቅ በኋላ የእግርኳስ ፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ጁነይዲ በሻ በተገኙበት የሽልማት ስነ-ስርአት የተካሄደ ሲሆን ሽልማቶቹም የሚከተሉት ናቸው፡፡
ደረጃ
1ኛ. የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ – 100 ሺህ ብር
2ኛ. ደደቢት – 75 ሺህ ብር
3ኛ. ሀዋሳ ከነማ – 50ሲኅ ብር
ኮከብ ግብ አግቢ
ሽታዬ ሲሳይ ( የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ – 35 ግቦች ) – 15 ሺህ ብር
ኮከብ ተጫዋች
ሽታዬ ሲሳይ ( የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ )
ኮከብ አሰልጣኝ
ብርሃኑ ግዛው ( የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ )
ኮከብ ግብ ጠባቂ
ማርታ በቀለ (ዳሽን ቢራ)
ኮከብ ዳኛ
ዋና ዳኛ – ፍቅርተ ገነቱ
ረዳት ዳኛ – ወይንሽት አበራ