አዳማ ከነማ ምንም ድል ሳያስመዘግብ ከሴካፋ ተሰናበተ

 

ኢትዮጵያን ወክሎ ወደ ዳሬ ሰላም ያቀናው አዳማ ከነማ ዛሬ ባደረገው የምድቡ 3ኛ ጨዋታ በታንዛንያው አዛም 5-0 በሆነ ሰፊ ውጤት ተሸንፏል፡፡ አዳማ ከነማ ከዚህ ቀደም ባደረጋቸው ሁለት ጨዋታዎች በዩጋንዳው ካምፓላ ሲቲ አውቶሪቲ እና በደቡብ ሱዳኑ ማላኪያ የተሸነፈ ሲሆን ዛሬ ያስመዘገበው ሽንፈትም በኢትዮጵያ ክለቦች የሴካፋ ተሳትፎ ታሪክ ከፍተኛው ሽንፈት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

በዘንድሮው ክረምት ወላይታ ድቻን ለቆ አዳማ ከነማን የተቀላቀለው እሸቱ መና በጨዋታው በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል፡፡

አዳማ ከነማ የዘንድሮውን ጨምሮ ለ2 ጊዜያት በሴካፋ ክለቦች ቻምፒዮና ቢሳተፍም ከ6 ጨዋታዎች 1 አቻ ብቻ በማስመዝገብ በሌሎቹ ተሸንፏል፡፡ አምና በተመሳሳይ ወቅት በአዛም 4-1 በሆነ በሰፊ ውጤት የተሸነፈ ሲሆን ዘንድሮም ታንዛንያው ቻምፒዮን በሰፊ ውጤት ተሸንፏል፡፡

 

ያጋሩ