ኢትዮጵያ በቅድመ ማጣርያው ሳኦቶሜን ትገጥማለች

ዛሬ በሩስያዋ ከተማ ፒተርስበርግ በወጣው የ2018 የአለም ዋንጫ ማጣርያ ድልድል መሰረት ኢትዮጵያ በቅድመ ማጣርያው ሳኦቶሜ ፕሪንሲፔ ደርሷታል፡፡

ኢትዮጵያ ኦክቶበር 5 ከሜዳዋ ውጪ እና ኦክቶቨር 13 ደግሞ በሜዳዋ የምታደርጋቸውን የደርሶ መልስ ጨዋታዎች አሸንፋ ካለፈች በሁለተኛው ዙር ቅድመ ማጣርያ ሪፑብሊክ ኦፍ ኮንጎን (ኮንጎ ብራዛቪል) ትገጥማለች፡፡

ሪፑብሊክ ኦፍ ኮንጎ በቀጥታ ወደ 2ኛው የማጣርያ ዙር ካለፉት ሃገሮች ዝቅተኛ ግምት የሚሰጣት መሆኗ ኢትዮጵያ ወደ ምድብ ማጣርያው የመግባት ተስፋዋን ከፍ ያደርግላታል፡፡

ዛሬ የወጣው የማጣርያ ድልድል ይህንን ይመስላል ፡- (ምስል @FIFAWorldCup )

 

Round 1
Round 1

 

Round 2
Round 2
ያጋሩ