የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል

ዛሬ ባህር ዳር ላይ በተካሄደው የዓለም ከ20 ዓመት በታች የሴቶች የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታ የካሜሮን አቻውን አስተናግዶ የነበረው የአኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን 2ለ1 በሆነ ውጤትአሸንፏል፡፡ ያውንዴ ላይ 0ለ0 የተለያየው ብሄራዊ ቡድኑ በባህር ዳሩ ግጥሚያ በሎዛ አበራ ሁለት ግቦች ታግዞ ወደ ቀጣዮ ዙር አልፏል፡፡ ሎዛ ግቦቹን በመጀመሪያው እና ሁለተኛው አጋማሽ አስቆጥራለች፡፡ ፓፑዋ ኒው ጊኒ ለምታዘጋጀው የዓለም ከ20 ዓመት በታች የሴቶች የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የኢትዮጵያ ቀጣይ ተጋጣሚ የአልጄሪያ እና ቡርኪና ፋሶ አሸናፊ ይሆናል፡፡

ያጋሩ