ፋሲካ አስፋው ኢትዮጵያ ቡናን ለቀቀ

ፋሲካ አስፋው ውል ማቋረጫውን ከፍሎ ከቡና መልቀቁን ክለቡ በይፈዊ የፌስ ቡክ ገፁ አስታውቋል፡፡

ከ1995 እስከ 1997 እንዲሁም በድጋሚ ከ2004 እስከ ዘንድሮው የውድድር ዘመን ማብቂያ ለኢትዮጰያ ቡና የተጫወተው አማካዩ ፋሲካ አስፋውን መልቀቅ ክለቡ ያስታወቀው እንዲህ ባለ መልክ ነው፡፡

‹‹ ከታዳጊ ቡድኑ ጀምሮ እስከ ዋናው ቡድን ቡናን በመሃል መስመር ተጫዋችነት አገልግሏል፡፡ በቡና ማሊያ ለብሄራዊ ቡድኑም ተመርጦ የመጫወት እድሉን አግኝቷል፡፡ 19 ቁጥር ለባሹ ፋሲካ አስፋው በ2005 .ም ለቡና በክለቡ ታሪክ ሪከርድ በሆነ የፊርማ ብር ውሉን ለሁለት አመት አራዝሞ ነበር፡፡ ዘንድሮ ግን ባቀረበው የመልቀቅ ጥያቄ ከወሰደው የፊርማ ብር ውስጥ 400000/አራትመቶሺህብር/ በመመለስ ውሉን አቋርጧል፡፡ ቡና ልጁን ላለመልቀቅ እና ችግሮችም ካሉ በጋራ ለመፍታት ፍላጎት እንዳለው ቢገልፅለትም በተጫዋቹ ጥያቄ መሰረት በስምምነት ለመልቀቅ ተገዷል፡፡ ››
ፋሲካ አስፋው ቡናን መልቀቁን ተከትሎ በተለያዩ ክለቦች እይታ ውስጥ ገብቷል፡፡ ዳሽንቢራ ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ደደቢት የተጫዋቹ ፈላጊዎች ናቸው፡፡

ያጋሩ